በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የወይራ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነው ሱራፌል አያና 99.9% በማምጣት 1ኛ ሆነ፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ተማሪ ሱራፌል አያና በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ በአማርኛ ቋንቋ ከሚማሩ ተማሪዎች መካከል 99.9% በማምጣት በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል 1ኛ ሆኗል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመንግሥትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ 85,219 ተማሪዎች መካከል የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነው ሱራፌል አያና 99.9% በመምጣት ተሸላሚ ሆኗል፡፡
በ2016 ዓ.ም በ8ኛ ክፍል ከተማ ቀፍና ክልል አቀፍ በተሰጠው ፈተና ቁጥራቸው 85,219 የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው የሚታወስ ሲሆን የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በልዩ ልዩ ስልጠናዎች የሥነልቦና እና ሁለንተናዊ ዝግጅት በማድረግ ለፈተና መቅረባቸው ከፍተኛ ውጤት እንዲያስመዘግቡ አስተዋጽ ማድረጉ ታውቋል፡፡
ተማሪ ሱራፌል አያና በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ በየዓመቱ በትምህረቱም ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በርካታ ሽልማቶችን ተሸላሚ እንደነበር ይታወቃል፡፡