አቧሬ ቅርንጫፍ በአራዳ ክፍለ ከተማ 1ኛ በመሆን ተሸላሚ ሆነ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አቧሬ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በአራዳ ክፍለ ከተማ ሥር ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 100% በማሳለፍ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳር ትምህርት ጽ/ቤት አዳራሽ የእውቅና እና ሽልማት ሥነ- ሥርዓት ላይ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አቧሬ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በክፍለ ከተማው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች በተሻለ ተማሪ ብዛት እና 100% ተፈታኞችን በማሳለፍ 1ኛ በመሆን የዋንጫ እና የሰርተፍኬት ሽልማት የተበረከተለት፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በተጠናቀቀው የ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል በከተማ እና በክልል በነበሩ ሚኒስትሪ ፈተናዎች 1ኛ በመውጣት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ሽልማት የተበረከተለት መሆኑ ይታወሳል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0930-36-37-79 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::