አክሲዮን ማኅበሩ ለመካከለኛ ደረጃ ሥራ መሪዎች ሥልጠና ሰጠ፡፡

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለርዕሳነ መምህራን፣ም/ርዕሳነ መምህራን እና ለትምህርት ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎችና የትምህርት ባለሙያዎች የተሳተፉበት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

Esdros

የስልጠናውን መጀመር በንግግር የከፈቱት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የኮርፓሬት የሰው ሀብት አስተዳዳር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘሪሁን አድማሱ “ይህንን ስልጠና መስጠት ያስፈለገው በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶችና በሥራ ክፍሎች የሚገጥሙን የአሠራር ችግሮች ለመፍታት እና ከሀገሪቱ ሕግና ከኩባንያው እሴቶች ጋር በማጣጣም ውጤታማ የአሠራር ሥርዓት ለመዘርጋት ነው ፡፡” በማለት የስልጠናውን መጀመር አብስረዋል፡፡
መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ.ም በዘሀብ ሆቴል የሥራ መሪዎች በስራ ሂደት የሀገሪቱን የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ፣ የኩባንያውን የሰው ሀብት መመሪያን እንዲሁም በሰራ ላይ አስተዳደራዊ ችግር በሚፈጠርበት ወቅት ችግሮችን የሚፈቱበት ስልት ላይ ያተኮረ ምቹና ጤናማ የሥራ ሂደትን ለማቀላጠፍ ያለመ የሥነ-ምግባር ጥሰት እርምጃዎች አፈጻጸምና የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ“ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት የኩባንያው የዳሬክተሮች ቦርድ ፀሐፊ አቶ ጌታነው ሙንዬ፣አቶ ዘርሁን አድማሱ የኮርፓሬት የሰው ሀብት አስተዳዳር መምሪያ ሥራ አስኪያጅ እና አቶ ሰለሞን ታደሰ የሎጀስቲክ መምሪያ ኃላፊ እና የሰራተኞች ቅሬታና የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው፡፡
በስልጠናው ቁጥራቸው 55 የሚደርሱ ርዕሳነ መምህራን፣ም/ርዕሳነ መምህራን ፣ የትምህርት ዘርፍ የሥራ ኃላፊዎችና የተወሰኑ ኤስክፐርቶች የተሳተፉ ሲሆን ከፍተኛ ውይይት እና ተሳትፎ የታየበት ስልጠና ነበር፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0930-36-37-79 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገጽ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::