አክሲዮን ማኅበሩ ለሥራ አመራር አባላት ሥልጠና ሰጠ፡፡
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ኮርፓሬት የሰው ሀብት አስተዳደር ከዲቮትድ ኮንሰልቲንግ ድርጅት ጋር በመተባበር ለሥራ አመራር አባላት በዮድ አቢሲኒያ ኢንተርናሽናል ሆቴል የተቋማዊ አሰራር ባህል/Corporate Culture/በሚል ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ግንቦት 23 እና 24 ቀን 2015ዓ.ም ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘርሁን ክብረት ስልጠናውን በሚመለከት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በስልጠናው ማጠቃለያም ላይ ሰልጣኞች በቀጣይ ሊጠቀሙበት ይገባል ያሉትን መልክት አስተላልፈዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የዲቮትድ ኮንሰልቲንግ ማኔጂንግ ዳሬክተር መራሔ ትጉሃን ዶ/ር ሙላቱ መብራቴ “በስልጠናው ሙሉ ተሳታፊ ሰልጣኞች የነበሩበት እና እኔም በጣም ደስተኛ ሆኜ ከሰጠሁት ስልጠናዎች አንዱ የእናንተ ተቋም በመሆኑ ወደፊትም ከድርጅታቹ ጋር አብሬ በመስራቴ እና በቀጣይም አብሮ ለመስራት ያለኝን ፍላጎት እየገለጽኩ በነበረው የስልጠና ቆይታችን በጣም ደስተኛ ነኝ “ በማለት ሀሳባቸውን ገልጸዋል፡፡
የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ኮርፖሬት የሰው ሀብት አስተዳደርም በ2015ዓ.ም ከያዛቸው የስልጠና መርሀግብራት መካከል ይህንን ስልጠና ጨምሮ በ31 የስልጠና ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከ3845 በላይ የስልጠና ተሳታፊዎችን ማሰልጠን መቻሉን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Esdros S.C, [6/10/2023 11:32 AM]
በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ ጥናትና ምርምር ሴሚናር ተካሔደ፡፡
በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአቧሬ ቅርንጫፍ 2ኛ/ደ/ት/ቤት የ2015ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተማሪዎች አምስት በተለያዩ ርዕሶች ዙሪያ የተዘጋጁ የጥናትና ምርምር ስራዎችን አቅርበዋል፡፡
በጥናትና ምርምር ሥራዎች ከቀረቡት ርዕሶች መካከልም 1ኛ የግእዝ ቋንቋን ለምን ለመማሪያነትና በትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ለተግባቦት አንጠቀምም?፣2ኛ በአቡነ ጎርጎርዮስ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት (አዋሬ ቅርንጫፍ) የአማርኛ ቋንቋ መመሪያ መፅሐፍ ከመጽሕፍ ዝግጅት አንፃር ተጠባቂነት ብሎም በተማሪው ላይ የታየው የጽሕፈት ችሎታ ግቡንመቷል ማለት ይቻላል ወይ? 3ኛ በአ/ጎ/2ኛ/ደ/ት/ቤት/አ/ቅ በጠዋትና በከሰዓት ትምህርት ክፍለ ጊዜያት የተማሪዎች ትምህርት አቀባበል እና ፍላጎት እንዴት ይታያል?4ኛ የአ/ጎ/2ኛ/ደ/ት/ቤት/አ/ቅ ከስድስት ዓመታት በፊት እና አሁን ያለበት ሁኔታ?፣እና 5ኛ የአ/ጎ/2ኛ/ደ/ት/ቤት/አ/ቅ የማህበራዊ ሳይንስ ትምህርት ዝግጅት እና የዓመቱ ሀገር አቀፍ የብሔራዊ ፈተና ውጤት ከተፈጥሮ ሳይንስ ጋር ሲነጻጸር በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮችን የያዙ የጥናት ጽሑሁፎች ቀርበዋል፡፡
ይህንን መሰል የጥናት መድረክ የትምህርት ዘርፉን ለማገዝ እና በቀጣይ ሊሻሻል እና ሊተገበሩ የሚገባቸው ጉዳዮችን የሚያመላክት በመሆኑ በግብአትነት እንደሚያገለግል ፤ መሰል መርሀግብራትም ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው በመርሀግብሩ የተገኙት ተሳታፊዎች ሀሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡
በመርሀግብሩ በትምህርት ዘርፍ የትምህርት ኤክስፐርቶች፣ የትምህርት አስተዳደር አካላት፣ መምህራን እና በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአቧሬ ቅርንጫፍ 2ኛ/ደ/ት/ቤት ተማሪዎች መርሀግብሩን ታድመዋል፡፡
የዘንድሮ 12 ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ያቀረቡት የጥናት መርሀግብር በአባቶች ጸሎት እግዚብሔርን በማመስገን የተጀመረ ሲሆን በመርሀግብሩም የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ተማሪዎች የመዝሙር እና የግጥም ዝግጅቶች የቀረቡበት እንደነበር ከአዋሬ ቅርንጫፍ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡