አዳዲሶቹ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለ2016 ዓ.ም ሥራ ይጀምራሉ፡፡

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰንሻይን ቅርንጫፍ ለ2016 ዓ.ም አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
በቅድመ መደበኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ለመስጠት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኘው ሰንሻይን ቅርንጫፍ ቁጥራቸው ከ1ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡
በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች 26ኛ እና 27ኛ ቅርንጫፍ በመሆን የተከፈተው የሰንሻይን ቅርንጫፍ ለ2016 ዓ.ም ሥራ መጀመር የሚያስችለውን የማስተማር ፍቃድ ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ያገኘ በመሆኑ በይፋ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ሥራ መጀመሩ ታውቋል፡፡

abune Gorgorious