ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለአዳዲስ ሠራተኞች ሥልጠና ሰጠ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ኮርፖሬት የሰው ሀብት አስተዳደር 84 አዳዲስ ሠራተኞች በግሎባል ሆቴል ነሐሴ 17 እና 18 ቀን 2015 ዓ.ም Induction and Socialization ፕሮግራም ያካሄደ ሲሆን በዚህም በ Organizational Awareness and Specific Orientation, Generic Competency for Effective Service Delivery and Esdros’ Rules and Regulations በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
ለሁለት ቀናት በተዘጋጀው በዚሁ ስልጠና ላይ የተሳተፉት በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሥራ የሚጀምረው አቡነ ጎርጎርዮስ ሰንሻይን ቅርንጫፍ መምህራን እና ድጋፍ ሰጪ አካላት ሲሆኑ ስልጠናው የተቋሙን እሴት፣ ግብና አጠቃላይ ሁኔታ በመረዳት ሥራቸውን በቀላሉ እንዲያከናውኑ እንዲሁም በስራ ድርሻቸው ምን እንደሚጠበቅባቸው እውቀት እንዲኖራቸው ያለመ እንደነበር ታውቋል፡፡

የስልጠናውን መጀመር በንግግር የከፈቱት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ምክትል ሥራ አስኪያጅና የትምህርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ክብረት “እንኳን ደህና መጣቹሁ!” በማለት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን ሰልጣኞች የኩባንያውን አጠቃለይ ባሕርይ በመረዳት በቀጣይ በሥራ ሂደት ሊያውቋቸውና ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ዐበይት ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ ስልጠናው ኤስድሮስን ይበልጥ የሚያውቁበት እንደሚሆንና የመማር ማስተማሩን ተግባር ለማከናወን የሚያስችል ክህሎትና አስፈላጊ መረጃ የሚያገኙበት እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ስልጠና የወሰዱትን 84 ሰልጣኝ ሠራተኞችን ጨምሮ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ከ1600 በላይ ሠራተኞች ያሉት መሆኑን ከኤስድሮስ ኮርፖሬት የሰው ሀብት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Esdros Construction