ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ከ 2017 ጀምሮ ለሚመራበት ስልታዊ ዕቅድ (Strategic Plan) ዝግጅት ግብዓት ለማግኘት ከዋና ዋና ባለአክሲዮኖች፣ ከቀድሞ እና አዲሱ የዳይሬክተሮች ቦርድ አመራር ጋር ወይይት አደረገ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ በቀጣይ ኩባንያው የሚመራበትን ስልታዊ እቅድ (Strategic Plan) በ18 የትኩረት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መርሀግብር በአኢንተር ሌግዥሪ ሆቴል የቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ ካላቸው ባለአክሲዮኖች እና የማኔጅመንት አባላት ጋር ሰፊና ጥልቅ ውይይት አድርጓል፡፡

Abunegorgorios

መርሀግብሩን በንግግር የከፈቱት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ አንተነህ ፈለቀ እንደተናገሩት “ከሁሉ አስቀድሜ ለሁለተኛ ዙር የኤስድሮስ ኮንሰትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ. እስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት በፎከስ ግሩፕ ዲስከሽን (Focus Group Discussion) ለመሳተፍ እንኳን በደህና መጣችሁ ለማለት እወዳለሁ፡፡የድርጅታችን የ ሁለተኛው ዙር እስትራቴጂክ እቅድ በማብቃቱ ፤ ሁለተኛውን እስትራቴጅክ እቅድ ማዘጋጀት አስፈላጊ በመሆኑ፤ የዳሬክተሮች ቦርድ ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መነሻነት አንድ የውጪ አማካሪ በመቅጠር እና በውስጥ አቅም ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የተዉጣጡ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች ያሉበት የእስትራቴጂክ እቅድ ዝግጅት ቡድን በማዋቀር የእቅድ ዝግጅት ሥራዉ ተጀምራል፡፡የድርጅታችን ባለድርሻ አካለት ከሆኑት መካከል እናንተ የድርጅታችን ከፍተኛ ባለ-አክሲዮኖች ዋነኞቹ ናችሁ፡፡ ከናንተ የሚገኘዉ የቡድን ውይይት (Focus Group Discussion) ፍሬ እጅግ አስፈላጊ ነዉ፡፡በመሆኑም፤ በተለይ (Globalization) እየፈጠረ ያለው ተጽዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ በውድድር ለመዝለቅ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንደስትሪ አ.ማ. አሁን እየሠራ ካለው አበይት ተግባራት በተጨማሪ ሌሎች የቢዝነስ ሀሳቦችን በማመንጨት ይበልጥ መሥራት ይጠበቅበታል፡፡” በማለት ንግግር በማድረግ መርሀግብሩን አስጀምረዋል፡፡

ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ ውይይት በቀጣይ ኤስድሮስ የሚመራበትን ስልታዊ ዕቅድ (Strategic Plan) በውጪ ኮንሰልታንትና በኩባንያው ባለሙያ በጥምረት ዝግጅት እየተዘጋጀ ሲሆን የዚህ ግባአት የማሰባሰብ ስራው በዋናነት ከኩባንያው መሪዎችና ከፍተኛ የአክሲዮን ባላድርሻ ካላቸው ጋር በመሆኑ ከፍተኛ ግብዓት የሚገኝበት እንደሆነ ከወጪ ኮንሰልታንት አቶ አምሳሉ ከሰተም ሆነ በኩባንያው ባለሙያዎች የተሰጡ ሀሳቦች ያመለክታሉ፡፡

 

በመጨረሻም ኩባንያው በቀጣይ ለ2 ዓመታት በሚመራበት ስልታዊ እቅድ ዝግጅት እና ግብአት ማሰባሰብ መርሀግብር ሰፊ ውያያት እና ገንቢ ሀሳቦች የተገኘበት እንደነበር በመርሀግብሩ አቶ አንተነህ ፈለቀ ማጠቃለያ ላይ ገልጸዋል፡፡