ወይራ ቅርንጫፍ በክፍለ ከተማው 2ኛ በመሆን ተሸላሚ ሆነ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በተካሄደ የኢንስፔክሽን ምዘና አፈጻደም 2ኛ በመሆን ተሸልሟል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ኮልፌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በተካሄደው መርሐግብር ላይ ወይራ ቅርንጫፍ በክፍለ ከተማው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል ተሸላሚ መሆን ችሏል፡፡

በመርሐግብሩም ወይራ ቅርንጫፍ በክፍለ ከተማው በ6ኛ ክፍል በተማሪ ዮሐና ዮናስ እና በ8ኛ ክፍል በተማሪ ሱራፌል አያና ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ተማሪዎቹም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱም ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ተማሪ ሱራፌል አያና 99.9% በመምጣት በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከተፈተኑ 85,219 ተማሪዎች መካከል 1ኛ በመሆን ተሸላሚ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::