ዓለም አቀፍ የሥዕል ውድድር አሸናፊዎቹ ሽልማታቸውን ተረከቡ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሩሲያዊውን አንቶን ቼኾቭ ሥራዎችን ለመዘከር በስሙ በተሰየመው 12ኛው ዓለም አቀፍ የሥዕል ውድድር [International Children’s Art Contest “Anton Chekhov and Characters of His Works”] የሥዕል ውድድር ያሸነፉት ተማሪዎች ሽልማታቸውን ተረከቡ፡፡

የ14 ዓመቱ ተማሪ ትንሳኤ ደበላ ከ14-17 ዓመት የእድሜ ክልል ውድድር የቤላሩስና የቻይና ተወዳዳሪዎችን በማስከተል ሀገሩን ኢትዮጵያን በ1ኛ ደረጃ ፣ከ11-13 ዓመት የዕድሜ እርከን ተማሪ ሶስና ባንታምላክ በ2ኛነት እና ተማሪ ረድኤት ቴዎድሮስ በ3ኛነት ከቻይና፣ ቱርክ፣ ኦስትሪያና ቤላሩስ ተወዳዳሪዎች ጋር ቀርበው አሸናፊ መሆናቸው ይታወሳል፡፡
ጳጉሜ 2 ቀን 2016 ዓ.ም በሩሲያ የሳይንስ እና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ በተደረገው የሽልማት ሥነ ሥርዓት የማዕለኩ ባልደረቦች፣ተሸላሚዎች እና የተሸላሚ ወላጆች በዝግጅቱ ላይ የታደሙ ሲሆን ተማሪ ትንሳኤ፣ ተማሪ ሶስና እና ተማሪ ረድኤት በሥነስርዓቱ ላይ ተገኝተው ሽልማታቸውን ተረክበዋል፡፡
የሩሲያ የባህል ማዕከል በቀጣይም ከአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ጋር በሥነ ጥበብ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ አብሮ ለመሥራት ያለውን ፍላጎት በዝግጅቱ ላይ የማዕከሉ የሥራ ኃላፊዎች ገልጸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::