የስብሰባ ጥሪ : ለኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር በኢትዮጵያ የንግድ ሕግ አንቀጽ 418፤419 ፣ 423 እና 424 በአክሲዮን ማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 9 መሠረት የባለአክሲዮኖች 8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 7ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሑድ ታሕሳስ 11 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ግሎባል ሆቴል ይካሔዳል፡፡ ስለሆነም በስብሰባው ላይ በአካል ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻችሁ አማካኝነት እንድትገኙ በአክብሮት ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የ8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
-
-
- የ8ኛ መደበኛ የጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች ማጽደቅ
- አዳዲስ ባለ አክሲዮኖችን መቀበል
- የዲሬክተሮች ቦርድ የ2012 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ
- የውጭ ኦዲተር ሪፖርት መስማትና ማጽደቅ
- የዲሬክተሮች ቦርድ የ2013 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች መስማትና ማጽደቅ
- የ2012 በጀት ዓመት የትርፍ ክፍፍል ላይ መወሰን
- የዲሬክተሮች ቦርድ አባላት አበል ማጽደቅ
- የ8ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ
-
የ7ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች
-
-
- የ7ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች ማጽደቅ
- የአክሲዮን ማኅበሩን ካፒታል ማሳደግ
- የ7ኛ ድንገተኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ
-
ማሳሰቢያ
- በአካል ለሚገኙ ባለአክሲዮኖች የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ፖስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ እንዲይዙ፡፡
- ተወካዮች ሕጋዊ የውክልና ማስረጃ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ይዘው እንዲቀርቡ፡፡
- በኮቪድ 19 ምክንያት አዳራሹ መያዝ የሚችለው የተሳታፊዎች ብዛት ከመደበኛው ሩቡን ስለሆነ ባለአክሲዮኖች በውስን ሕጋዊ ወኪሎቻችሁ በኩል መሳተፍ እንድትችሉ ተገቢውን ውክልና እንድትሰጡና በጉባኤው ላይ የሚገኙ ሁሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እንድታደርጉ በአክብሮት መልእክታችን እናስተላልፋለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ
0930-363-779
0930-363-949
0118-688-450/51
በመጠቀም መደወል የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
የዲሬክተሮች ቦርድ
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አክሲዮን ማኅበር