የስነምግባር ሳጥኖች በኤስድሮስ

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የተገልጋዮችን ቅሬታ እና አስተያየት ለማወቅ የስነ-ምግባር ሳጥኖች በሁሉም ቅርንጫፎች በማስቀመጥ አስተያየቶችን እየሰበሰበ ይገኛል፡፡
የስነ ምግባር ሳጥኖቹ ማንኛውም ትክክል ያልሆነ የስነ-ምግባር ግድፈት፣ ህገወጥ ወይም የሚያጠራጥር እንቅስቃሴ እና ጠባይ በአክስዮን ማህበሩ ክንውኖች በሰራተኞች ፣ በተማሪዎች ፣በወላጆች እና በአቅራቢያ በሚገኙ አጋር ድርጅቶች የስራ ሂደት ላይ ሲታይ አስተያየት ለማድረግ እና ሁላችንም ልጆቻችን በስነምግባር የታነፁ እንዲሆኑ የበኩላችንን ለመወጣት የሚረዳ ነው፡፡
በመሆኑም ማንኛውም የድርጅቱ ሰራተኛ ሁልጊዜ የስነ-ምግባር ጉዳዮች ሲገጥመው መጀመሪያ ሊያነጋግረው የሚገባ የሚቀርበውን የስራ ኃላፊ ወይም የሰው ኃይል መምሪያ መሆን አለበት፡፡ ተማሪ ወይም ወላጅ ሆነው የስነ-ምግባር ጉዳዮች ወይም ቅሬታ ካጋጠመ ደግሞ ሁልጊዜ መጀመሪያ የትምህርት ቤቱን ርዕሰ መምህር ማነጋገር ሲችሉ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የበላይ ኃላፊ ድረስ ቅሬታን ማቅረብ ይቻላል፡፡

ሁልጊዜም ቅሬታ ሲኖር ድርጅቱ በአካል መጥተው እንዲያቀርቡ የሚያበረታታ ሲሆን ታዲያ የቀረበው ቅሬታ ላይ ክትትል ካልተደረገ እና ማንነት ሳያሳውቁ ማቅረብ ከተፈለገ ጉዳዩን በጽሁፍ በማስፈር በዚህ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡
ቅሬታ ያላቸው ሰራተኞች ፣ ተማሪዎች እና ወላጆች ቅሬታቸውን በአማርኛ ፣በግዕዝ ወይም በእንግሊዘኛ ቋንቋዎች በመጻፍ ሳጥኑ ውስጥ ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡
የስነምግባር ሳጥኑ ለሁሉም የድርጅቱ ሰራተኞች ፣ ለተማሪዎች እና ወላጆች በአጠቃላይ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን ከሰሞኑ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚገኙትን ሳጥኖች በመክፈት የተሰጡትን አስተያየቶች ለማወቅ ተችሏል፡፡
በመሆኑም ከሳጥኑ ውስጥ የተገኙ አስተያየቶችን በተመለከተ ድርጅቱ ማሻሻል የሚገባው ጉዳዮች ላይ የተሰጡ አስተያየቶች እንዳሉ እና በዚህም ዙሪያ ቦርዱ ተወያይቶ ለሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች አቅጣጫ ሰጥቷል፡፡ በመሆኑም ቦርዱ ቅሬታ የታየባቸውን በመውሰድ ለማሻሻል እንደሚሰራ እንዲሁም የተሰጡትን ጠንካራ ጎኖች ይዞ መቀጠል እንደሚገባ አስቀምጧል፡፡
እንደ ድርጅቱ አሰራር የተገኙት አስተያየቶች የሚከፈቱት የውስጥ ኦዲተሩ ከዋና ስራ አስኪያጁ ጋር በመሆን ነው፡፡ ሪፖርቱም በየመልኩ ተዘጋጅቶ ለዲሬክተሮች ቦርድ አባላት በማቅረብ ውይይት በማድረግ አቅጣጫ ይሰጥባቸዋል፡፡
በአጠቃላይ ቦርዱ ማንኛውም ቅሬታ እና አስተያየት ያለው ሰው በአካል መጥቶ ማቅረብ እንደሚችል ይህ ካልሆነ የስነምግባር ሳጥኖቹን በመጠቀም እንዲያቀርብ ሲያበረታታ በባለፈው አስተያየት በመስጠት ለተሳተፉ አካላትም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

የአክሲዮን ማህበራችንን ድህረ ገፅ https://esdros.com እንዲሁም ቴሌግራም https://t.me/Esdrossc በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ።