የትምህት ቤት ክፍያ ችግር ለገጠማቸው ተማሪዎች የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ተካሄደ፡፡

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ከወላጅ ኮሚቴ ጋር በመተባባር በትምህርት ቤት ክፍያ ምክንያት ተማሪዎች ትምህርት እንዳያቋርጡ የሚያስችል የገቢ ማስገኛ (ማሰባሰቢያ) መርሀግብር አካሄደ፡፡
ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ በተዘጋጀው በዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀግብር ተማሪዎች፣ የሚዲያ ባለሙያዎች፣ ወላጆች፣ የትምህርት እና የሥነልቦና ባለሙያዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች አካላት በዝግጅቱ ላይ ታድመዋል፡፡

Abunegorgorios

ዝግጅቱን የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ መምህራን እና የወላጅ ኮሚቴ በጥምረት ያስተናበሩት ሲሆን ለዝግጅቱ ድምቀት የሚሆኑ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ስራዎችን ያቀረቡበት፣ እንዲሁም ወላጆችና መምህራን የጥጥ መፍተል ውድድር የተሳተፉበት በገና ለጨረታ የቀረበበት፣የቃል መግቢያ ሰነድ እና የዝግጅቱ መግቢያ ትኬት ገቢዎች በማቅረብም ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ ስራዎች የተከናወኑበት ነበር፡፡

Abunegorgorios

በአጠቃላይ፣ ዝግጅቱን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡት የወላጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ፀሐይ እንደተናገሩት “ይህ ዝግጅት መነሻው ምክንያት በ2016ዓ.ም ለ13 ተማሪዎች የትምህርት ቤት ክፍያ ወጪ እና ለ9 ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የልዩ ፍላጎት መምህር እና የቴራፒ አገልግሎት ወጪ በአንድ በጎ አድራጊ ወላጅ ለመሸፈን የተጀመረውን በጎ ተግባር ለማገዝ እና ተጨማሪ ተማሪዎችን በ2017 የትምህርት ዘመን ይበልጥ ለመስራት በማሰብ የተዘጋጀ ዝግጅት ነው“ ብሏል፡፡ በሌላ መልኩ ”የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህርት ዝይን በበኩላቸው ”የመማር ማስተማር ሂደቱን ተማሪዎች እየተዝናኑ ወላጆች ደግሞ እየተማሩ ይህንን መልካም የበጎ አድራጎት ስራን ለመስራት እንደሚያስች ሰፊ ትምህርት እና ልምድ የወሰድንበት እንዲሁም ወደፊት በሌሎች ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ቢለመድ ተማሪዎችን የበለጠ ማገዝ የሚያስችል ስራ መስራት ያስችላል” ብለዋል፡፡
በቀጣይም ይህንን መሰል ስራዎችን ለመስራት መታቀዱን ከአዘጋጅ ኮሚቴው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Abunegorgorios