የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ተማሪ ተሸላሚ ሆነች፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተዘጋጀ የዕውቅና እና ሽልማት መርሀ-ግብር ላይ በ2016 ዓ.ም በ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና 99.9 % በማምጣት የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆነችው ተማሪ ብሌን ጥላሁን በከተማ ደረጃ ተሸላሚ ሆናለች፡፡

ነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ.ም በኢንተር ሌግዥሪ ሆቴል በተካሄደው 31ኛ የትምህርት ጉባኤ ማጠናቀቂያ መርሀግብር በከተማ ደረጃ በትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጾ ላበረከቱ አካላት በተዘጋጀው የሽልማት ስነስርዓት ተማሪ ብሌን በ2016ዓ.ም በተካሄደው ከተማ አቀፍ የ6ኛ ክፍል ፈተና ባመጣችው 99.9 % ውጤት የሜዳሊያና የታብሌት ተሸላሚ የሆነችው፡፡
ተማሪ ብሌን ጥላሁን ከዚህ በፊት በነበራት ከፍተኛ አስተዋጾ በወረዳ፣ በክፍለ ከተማ እና በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ሲካሄዱ በነበሩ የጥያቄና መልስ ውድድሮች አሸናፊ በመሆን የተለያዩ ሽልማቶችን ስታገኝ መቆየቷ ይታወሳል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::