የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ከ ቅድስት ሥላሴ ዩቨርሲቲ ጋር በመተባበር ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተናን ተፈትነው የዩኒቨርሲው ቆያታቸውን አጠናቀዋል፡፡ ይህንን ዋናውን የሀገር አቀፍ ፈተና አምሳያ (ሲሙሌሽን) ፈተና አጠቃላይ ሂደት በተለያየ ክፍል እንቃኛለን፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ላይ ባደረገው የደሰሳ ጥናት ባገኘው ግብረ መልስ ለ2015ዓ.ም ተፈታኞች ዋናውን የሀገር አቀፍ ፈተና አምሳያ (ሲሙሌሽን)የሞዴል መነሻን አንዱ ግብአት ሲሆን ሌሎችም መነሻዎችን እንቃኛለን፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ለመጀመሪ ጊዜ ከወላጅና ቤተሰብ ተነጥለው ለፈተና ወደ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቪርሲቲ በመግባት የዶርም ምደባ፣የካፌ ሰልፍ እና ምግብ፣የፈተና ወቅት በአጠቃላይ በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ምን እንደሚመስል እንቃኛለን፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የለቡ፣ሰሚት እና አቧሬ ቅርንጫፍ ትምህት ቤቶች የ2ኛ ደረጃ ርዕሳነ መምህራን ስለ ተማሪዎቻቸው የነበራቸውን ዝግጅት እና ቅድስት ሥላሴ ዩኒቪርሲቲ የነበራቸውን ቆይታ የምንቃኝበት፡፡
የ2015ዓ.ም ተፈታኞች ሲሙሌተር (ዋናውን የሀገር አቀፍ ፈተና አምሳያ)የሞዴል ፈተናን መጠናቀቅን በማስመልከት የመዝጊያ መርሀግብር ላይ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቪርሲቲ ፕሬዘዳንት እና የኤስድሮስ የቦርድ እና የማኔጅመንት አካላት፣የትምህርት ኤክስፐርቶች እና ርዕሳነ መምህራን በተገኙበት የተዘጋጀውን የማጠቃለያ መርሀግብር የምንቃኝበት ዝግጅቶችን ወደ እናንተ የምናደርስ ይሆናል፡፡

 

Abungorgorios