የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን መዝጊያ በደማቅ ዝግጀት ተከበረ፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ.ም የመዝጊያ መርሀግብ በታላቅ ድምቀት ሐምሌ 2 ቀን 2015 ዓ.ም በሁሉም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ተከብሯል፡፡
በዚሁ ዝግጅት ላይ የየትምህርት ቤቶቹ ርዕሳነ መምህራን የ2015 ዓ.ም ለበዓሉ ታዳሚዎች የትምህርት ዘመን ክንውናቸውን ሪፓርት ያቀረቡ ሲሆን በዓሉን በማስመልከትም የእንኳን አደረሳቹህ መልእክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
በመላው ሀገሪቱ በሚገኙት ትምህርት ቤቶች ቅጥር ግቢ በተካኔደው የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መዝጊያ ዝግጅት ላይ በትምህርት ዘመኑ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫ፣ የሜዳልያ ፣የሰርተፍኬት እና የተለያዩ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡በዚሁ ዝግጅት ላይም በሥነምግራቸው ከየትምህርት ክፍላቸው የላቀ ውጤት ያመጡ ምስጉን ተማሪዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
በመርሀግብሩም የመማር ማስተማር ሂደትን በብቃት ለመሩ መምህራን፣የአስተዳደር ሠራተኞች እና ድጋፍ ሰጪ የትምህርት ቤቶቹ አካላት የዕውቅና፣ የምስጋና፣ የሰርተፍኬት እና የሜዳልያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን መዝጊያ መርሀግብር የተማሪዎች የኪነጥበብ ዝግጅቶች፣ የመምህራን እና የአስተዳዳር አካላት የተለያዩ ዝግጅቶችን በማቅረብ በዓሉን አድምቀውታል፡፡በበዓሉ ማብቂያም ላይ የተማሪዎች የትምህርት ማሳወቂያ ካርድ ከየትምህርት ክፍሉ መምህራን ለተማሪዎች ተሰጥቷል፡፡
ሐምሌ 2 ቀን 2015ዓ.ም በተካሄደው በዚህ የትምህርት ዘመን የመዝጊያ መርሀግብር ላይ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንደስትሪ አ.ማ ተወካዮች፣የተማሪዎች ወላጆች፣የትምህርት ቤቶቹ መምህራን እና የትምህርት ቤቶቹ ማህበረሰብ በተገኙበት በታላቅ ድምቀት በማክበር አጠናቀዋል፡፡