የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ድሬደዋ ቅርንጫፍ በ8ኛ ክፍል በድሬደዋ ከተማ ቀዳሚ ሆነ፡፡

የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር በ2016 ዓ.ም በ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች መካከል የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ድሬደዋ ቅርንጫፍ ባስመዘገቡት ውጤት በድሬደዋ ከተማ ካሉ ትምህርት ቤቶች ቀዳሚ ውጤት አስመዝግቧል፡፡
የድሬደዋ አስተዳዳር ትምህርት ቢሮ ዓርብ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ ባደረገው የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የድሬደዋ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነችው ተማሪ ሶሊያና ካሳሁን ከተፈተነችው 6 የትምህርት ዓይነቶች ሁሉንም 100% በማምጣት በድሬደዋ ከተማ ካሉ 8ኛ ክፍል ትምህርት ቤቶች አሁን ባለው መረጃ ቀዳሚ መሆኗ ታውቋል፡፡

Abune Gorgorios   

ተማሪ ሶሊያና ካሳሁንን በመከተል ተማሪ ናሆም እሸቱ 98.89% እና ተማሪ ቤተልሄም ሶቤ 98.06% በማምጣት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ በመያዝ በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ድሬደዋ ቅርንጫፍ ከተፈተኑ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከለል ቀዳሚ ሆኗል፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ካሉት 27 የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች መካከል ድሬደዋ ቅርንጫፍ አንዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በቅድመ መደበኛ እና በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 980 ተማሪዎችን ተቀብሎ በ2016 ትምህርት ዘመን ሲያስተምር ቆይቷል፡፡                                                                                                                                                                                          

ለበለጠ መረጃ፡-
 በስልክ ቁጥር 0930 363 779 በመደወል ወይም/እና
 የአክሲዮን ማኅበራችንንድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::