የአዋሬ ቅርንጫፍ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ለመቅዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረጉ፡፡

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአቧሬ ቅርንጫፍ 2ኛ ደረጃ ትምህረት ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ከወላጆች፣ከመምህራን እና ከትምህርት ቤቱ ማኅበረሰብ ያሰባሰቡትን የገንዘብ እና የአልባሳት ድጋፍ ለመቅዶንያ የአረጋዊያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ድጋፍ አደረጉ፡:

Abune Gorgorios

የ2016ዓ.ም የ11ኛ ክፍል ተማሪዎቹ ግምቱ ከ19ሺ ብር በላይ የሚገመት የአልባሳትና የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ በማዕከሉ በመገኘት ያደረጉ ሲሆን በልገሳው ወቅትም ተረጂዎችን እና በማዕከሉ የሚገኙ ተረጂዎች የፈጠራ ስራዎች ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ልጋሰውን ያበረከቱት ተማሪዎች በማዕከሉን በጎበኙበት ወቅት ተዘዋውረው በተመለከቱት ነገር መደሰታቸውን የገለጹ ሲሆን ለሀገርና ለወገን ትልቅ አስታዋጽዖ ያበረከቱ ሰዎች በማዕከሉ እንደሚገኙ በመመልከታቸው ይህንን መሰል ልገሳ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ አዋሬ ቅርንጫፍ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ከዚህ ቀደም መሰል የበጎ አድራጎት ሥራዎችን በከተማው ለሚገኙ በርካታ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

Abounegorgorios