የ2016ዓ.ም የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ዘመን መዝጊያ መርሀግብራት ተካሄደ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ2016 ዓ.ም የትምህርት መዝጊያ መርሀግብ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት በሁሉም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ተካኔዷል፡፡
በመርሀግበሩ መክፈቻም የ2016 ዓ.ም በሁሉም የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ት/ት ቤቶቻችን የመማር ማስተማር ስራ ሪፓርት በርእሳነ መምህራን አማካኝነት የቀረበ ሲሆን የወላጅ ኮሚቴም በትምህርት ዘመኑ ያከናወኑትን ዋናዋና ስራዎች አቅርበዋል፡፡

Abunegorgorios

እሁድ ሰኔ 30 ቀን 2015 ዓ.ም በተካሄደው በዚሁ የትምህርት ዘመን የመዝጊያ መርሀግብር ላይ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንደስትሪ አ.ማ የማኔጅመንት ዓባላት፣ የተማሪ ወላጆች፣የትምህርት ቤቶቹ ማህበረሰብ እንዲሁም ተማሪዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት የተከበረ ሲሆን የትምህርት ዘመን መዝጊያ መርሀግብር ስርዓቱን የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የኪነጥበብ ዝግጅቶች፣ የበገና ድርደራ እና የመምህራን የግጥም ስራዎችን በማቅረብ ዝግጅቱን አድምቀው አክብረዋል፡፡

Abunegorgorios

በ27 የአቡነ ጎርጎሪዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቻችን በተካሄደው የመዝጊያ መርሀግብር ላይ በትምህርት ዘመኑ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የዋንጫ፣ የሜዳልያ ፣የሰርተፍኬት እና የተለያዩ ሽልማቶችን በ ኤስድሮስ አ/ማህበር አመራር እና በትምህርት ቤቶች አስተዳደር አካላት ተበርክቶላቸ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በመማር ማስተማር ስራው ከፍተኛ አሰተዋጾ የነበራቸው መምህራን፣ የአስተዳዳር ሰራተኞች፣ ድጋፍ ሠጪ ሰራተኞችም ጭምር ልዩ ልዩ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Abune gorgorios