የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሥነልቦና እና አባታዊ ምክር መርሀግብር ተካሄደ፡፡

በ2016 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 4 ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የሥነልቦና ስልጠና እና አባታዊ ምክር የሚለግስ መርሀግብር ተካሄዷል፡፡

መርሀ-ግብሩን በንግግር የከፈቱት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትረ አ.ማ የዳሬክተሮች ቦርድ አባልና የትምህርት ዘርፍ ክትትልና ድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ይሁኔ ”ተማሪዎቻች ለሀገር አቀፍ ፈተናው ሰፊና በቂ ዝግጅት እንድታደርጉ በርካታ ስራዎች ተሰርቷል፡፡ በተለይም በ 2016 የ12 ክፍል ቢሄራዊ ፈተና በበየነመረብ (ኦንላይን) መሆኑን ታሳቢ በማድረግ በርካታ ፈተናዎችና ሞዴሌችንም ጭምር በበየነመረብ (ኦንላይን) እንድትወስዱ በማድረግ ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ በመሆኑም ይህ የዛሬው መርሀግብር ስታደረጉት የነበረውን ሁለንተናዊ ዝግጅት በስነልቦና የተደገፈ እንዲሆን እንዲሁም በአባቶች እንድትባረኩ ለማድረግ ነው” በማለት የመርሀግብሩን መከፈት አብስረዋል፡፡
ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በተካኔደው በዚህ መርሀግብር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በሀገር አቀፍ ፈተና ሊገጥማቸው የሚችሉ ጉዳዮች እና አስቸጋሪ ሁኔታዎችን መፍታት የሚያስችል የሥነልቦና ዝግጅት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠናና አባታዊ ምክር ያገኙበት ነበር፡፡

በመርሀግብሩም የ2016 ዓ.ም የሀገር አቀፍ ፈተናውን አጠቃላይ ሁኔታ በተመለከተ አቶ እያሱ ታዬ በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትረ አ.ማ ጊዜያዊ ም/ዋ/ሥ/አስኪያጅ ትምህርት ዘርፍ አስገንዝቧል፡፡ በሌላ መልኩ በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የሰሚት 2ኛ ደረጃ ርዕሰ መምህር ጣሳቸው ጫኔ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

 

በመጨረሻም በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትረ አ.ማ የስራ ባልደረባ ቀሲስ ክፍሉ ወ/ሐዋሪያ ለተማሪዎቹ ምክር፣ አባታዊ ቡራኬና ፀሎት በማድረግ ተማሪዎቹን ለፈተናው ከስነ ልቦና እስከ መንፈሳዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ምክር ሰጥቷል፡፡