የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገለጸ፡፡

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በሁሉም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ሰኔ 4 እና 5 ቀን 2016 ዓ.ም ለ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እና ከሰኔ12 እስከ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ከተማ አቀፍ የ6ኛ ክፍል ፈተና ለመፈተን ተማሪዎች ሙሉ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ተማሪዎቹ ለ2016 ዓ.ም የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ለሆነው ፈተና የሥነልቦና እና ሁለንተናዊ ዝግጅት በማድረግ ዝግጅታቸውን ማጠናቀቃቸው ተገልጿል፤ለዚህም በዋናው ቢሮ እና በቅርንጫፍ ት/ቤቶች በርካታ ተግባራት የተከናወኑ ሲሁን ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡
ተማሪዎቹ ለፈተና ዝግጅት ከሥነ-ልቦና አንጻር ስልጠና የወሰዱ ሲሆን በማጠናከሪያ የትምህርት መርሐግብርም በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡የተማሪዎችን የዝግጅት ደረጃ የሚለኩ የጥያቄና መልስ ውድድሮች በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ደረጃ እና በየቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቹ 2 ጊዜ ተካሂደዋል፡፡ በኤስድሮስ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል እና የትምህርት ኤክስፐርቶች በጋራ ባዘጋጁት ኦንላይን /Online/ ፈተና እንዲሠሩ በማድረግ ጭምር ሁለንተናዊ ዝግጅት መደረጉ ታውቋል፡፡

Aboune Gorgorios

በ7 የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የ8ኛ እና 6ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተናው ሁለንተናዊ ዝግጅት ማድረጋቸውን ከኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ዘርፍ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በዚህ ክልል አቀፍ ሆነ ከተማ አቀፍም ፈተና የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከግል የትምህርት ተቋማት መካከል ቀዳሚ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ: