የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በሚኒስትሪ ከፍተኛ ውጤት አስመዘገቡ
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ2015ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ተፈታኝ ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ታሪክ ሠርተዋል፡፡
ሰኔ 26 እና 27 ቀን 2015 ዓ.ም በተሰጠው የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አምስት ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች 625 ተማሪዎችን ማስፈተናቸው ታውቋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ይፋ በተደረገው ውጤት መሠረት በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የአዋሬ፣ የለቡ፣ የወይራ፣ የሲኤምሲ እና የቃሊቲ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ካስፈተኗቸው 625 ተማሪዎች ውስጥ አማካይ ውጤታቸው (ጥሬ ማርካቸው) ከ90% በላይ ያመጡት 53 ተማሪዎች፣ከ80-89.9% ያመጡት 183 ተማሪዎች፣ ከ70-79.9% ያመጡ ተማሪዎች 231 ሲሆኑ ቁጥራቸው 158 የሚሆን ተማሪዎች ማለትም 25% የሚሆኑ ተማሪዎች አማካይ ውጤታቸው 70% እና ከዚያ በታች መሆኑን ከኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ዘርፍ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በአሁኑ ወቅት 17ሺህ ተማሪዎችን እያስተማረ የሚገኘው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2016 ዓ.ም ተቀብሎ የሚያስተምራቸውን የተመሪዎች ቁጥር ከ 18 ሺህ በላይ በማሳደግ አገልግሎቱን ተደራሽ እንደሚያደርግ ይጠበቃል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::