4ኛው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የፈጠራ ሥራና ዐውደ ርእይ በታላቅ ድምቀት ተከፈተ!

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የትምህርት ዐውደ ርእይ እና የፈጠራ ሥራዎች ውድድር መርሀግብር ከዛሬ አርብ መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ እሁድ መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ለጎብኚዎች ክፍት ይሆናል፡፡

Abune Gorgorious

በዚሁ ለ4ኛ ጊዜ በሚካሄደው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በኪነጥበብ፣ የተማሪ የፈጠራ ሥራ፣ ICT፣ ሥዕልና ቅርጻቅርጽ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
በአዲስ አበባ የሚገኙት 18 የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የሚሳተፉበት ይህ አውደ ርዕይና የፈጠራ ስራዎች የሚቀርቡበት መድረክ በመርሀግብሩ ማጠቃለያ ላይ የዋንጫ፣የሜዳልያና የሰርተፍኬት ተሸላሚ እንደሚሆኑ ይጠበቃል፡፡

Abune Gorgorios

በዐውደ ርእይ እና የፈጠራ ሥራዎች ውድድር አሸናፊዎች ሽልማት ተበረከተላቸው

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የትምህርት ዐውደ ርእይ እና የፈጠራ ሥራዎች ውድድር መርሐግብር ዓርብ መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ ተከፍቶ ለ3 ተከታታይ ቀናት ለዕይታ በመብቃት በበርካታ እንግዶች፣ወላጆች ፣መምህራን እና ተማሪዎች ተጎብኝቷል፡፡
በዚሁ ለ4ኛ ጊዜ በተካሄደው የትምህርት ዐውደ ርእይ እና የተማሪዎች የፈጠራ ሥራ በኪነጥበብ፣ የተማሪ የፈጠራ ሥራ፣ ICT፣ ሥዕልና ቅርጻቅርጽ፣ የተቋሙ እሴት እና ዲኮረሽን (የተሰጠህን ቦታ ማሸብረቅና ማስዋብን) ዘርፍ ላይ ውድድር የተካሄድበት ሲሆን ከመጋቢት 20 እስከ 22 ቀን 2016 ዓ.ም የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች 27ኛ ቅርንጫፍ በሆነው ሰንሻይን አጸደ ሕፃናትና 1ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ተካሄዷል፡፡

Abune Gorgorios

መርሐግብሩን በንግግር የከፈቱት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ፈለቀ ናቸው፡፡ “ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ይህ አውደ ርእይና የፈጠራ ስራዎች ውድድር የተቋሙን እሴት የሚያሳይ አዲስ የመወዳደሪያ ርእስን በማካተት ከዚህ ቀደም ከነበሩት ዝግጅቶች በተለየ መልኩ የተዘጋጀ ነው፡፡” በማለት ንግግር ያደረጉት ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ አንተነህ ፈለቀ ለዚህ ዝግጅት መሳካት አስተዋጽዖ ያደረጉትን አካላት አመስግነዋል፡፡
በመርሐግብሩ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙት 18 ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የተሳተፉበት ሲሆን በፈጠራ ስራዎች፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በኪነጥበብ ዘርፍ በርካታ የፈጠራ ሥራዎች ቀርበው ከፍተኛ ውድድር የተካሄደባቸው ሥራዎችም ቀርበዋል፡፡
ለ3 ተከታታይ ቀናት ለእይታ በቆየው በዚህ ዐውደ ርእይ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው የኩባንያው የቦርድ እና ማኔጅመንት አመራሮች፣እንግዶች፣ ወላጆች፣ መምህራን እና ተማሪዎች የጎበኙት ሲሆን የፈጠራ ስራዎችን በመዳኘት የኢንፎርሜሸን ቴክኖሎጂ ባለሙያች፣ታላላቅ አርቲስቶች እና በርካታ ባለሙያዎችና ኤክስፐርቶች ተሳትፈውበታል፡፡

መጋቢት 22 ቀን 2016 ዓ.ም በመረሐ ግብሩ መዝጊያ ላይ በፈጠራ ሥራ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችና አሸናፊ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ከኤስድሮስ የዳሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ከማኔጅመንት አባላትና ከዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ከአንተነህ ፈለቀ እጅ የዋንጫ፣የሜዳሊያና የሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ዐውደ ርእይ እና የፈጠራ ሥራዎች ውድድር ከፍተኛ ፉክክር እና አስደማሚ ትዕይንቶች የታዩበት ነበር፡፡
የተቋም እሴት ላይ በተካሄደ ውድድር ከቅድመ አንደኛ በግል 1ኛ. ልዕልና መስፍን ከለቡ፣ከእግዚአብሐር አብ 2ኛ. የአብ ቴዎድሮስ እና 3ኛ. ማህሌተ ጽጌ ከሲኤምሲ ሲያሸንፉ በዚሁ ዘርፍ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በግል ከለቡ ቅርንጫፍ 1ኛ ተማሪ ህሊና ናርዶስ ፣ከቃሊቲ ቅርንጫፍ አማኑኤል ዮሐንስ እና ፍሬፅድቅ ሄኖክ 2ኛ. እና3ኛ. በመሆን አሸንፈዋል፡፡ ከሁለተኛ ደረጃ በግል፣1ኛ. ሳሮን ሳሙኤል ከአዋሬ፣ከለቡ 2ኛ. ዮሐንስ ወርቁ እና 3ኛ ቃለአብወርቁ ከቃሊቲ እሸናፊ ሆኗል፡፡
በሳይንስና ፈጠራ ዘርፍ በግል በተደረገ ውድድር ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1ኛ ከለቡ የሳይንስ መርጃ መሣሪያ በመስራት፣2ኛ ከእግዚአብሐርአብ የሂሳብ መርጃ መሣሪያ እና 3ኛ ከሲኤምሲ የቋንቋ መርጃ መሣሪያ አሸናፊ ሲሆኑ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1ኛ. ዮናታን ደጀኔ ከሰንሻይን፣2ኛ. ያፌት አብዮት ከወይራ እና 3ኛ. እነ ሶሊያና ተክላይ ከሲአምሲ አሸናፊ ሆነዋል፡፡ ከ2ኛ ደረጃ በሳይንስና ፈጠራ ዘርፍም1ኛ. አናኒያ ባያብል ከሰሚት፣2ኛ. እነ ሚልካ ጫላ ከቃሊቲ እና 3ኛ ልዑል ሲሳይ ከአዋሬ አሸናፊ ሆኗል፡፡
በአይሲቲ ፈጠራ ዘርፍ በግል በተደረገ ውድድር ከአንደኛ ደረጃ 1ኛ ናሆም ሰለሞን ከእግዚአብሔርአብ፣2ኛ. ያሬድ ኤፍሬም ከለቡ እና 3ኛ. ጥበቡ ሙሉቀን ከቃሊቲ ያሸነፉ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1ኛ. ዳግማዊ እንዳልካቸው ከአዋሬ ፣ 2ኛ በርናባስ ከለቡ እና 3ኛ. በረከት ታደሰ ከቃሊቲ በዘርፉ አሸናፉ ሆነዋል፡፡
በኪነጥበብ የፈጠራ ሥራ ዘርፍ በግል ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል በተደረገ ውድድር 1ኛ ናታኔም አዲስ ከአዋሬ በመነባንብ ፣ 2ኛ. አሜን አቤል ከአዋሬ ግጥም እና 3ኛ. ሶሊያና ወልዴ ከሲ.ኤም.ሲ መነባንብ ሲያሸንፉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 1ኛ. ትምኒት አንበሴ ከለቡ መነባንብ፣2ኛ. ቤዛ ዮሐንስ ከለቡ ግጥም ፣ ተማሪ ሄርሜላ ጎሳ ከሰሚት ግጥም እና ተማሪ መክሊት ተስፋዬ ከአዋሬ እኩል 3ኛ በመውጣት በግጥም ዘርፍ አሸናፊ ሆነዋል፡፡
በሥዕልና ቅርፃቅርጽ ዘርፍ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1ኛ. እነ ሴማ ዳዊት ከሲኤምሲ 2ኛ. ተማሪ ዲቦራ ከሰንሻይን እና 3ኛ. ትንሳኤ ዳባ ከለቡ አሸናፊ ሲሆኑ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1ኛ. እነ ፍቅረማርያም ቀፀላ፣2ኛ. ሚካኤላ ያፌት ከለቡ እና 3ኛ. ጽዮን ፍሬው ከአዋሬ ሆነዋል፡፡

Abune Gorgorios

በአጠቃላይ ውጤት የተቋም እሴት ዘርፍ ላይ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ 1ኛ. ለቡ ቅርንጫፍ ፣ 2ኛ እግዚአብሔርአብ ቅርንጫፍ እና ሃያሁለት ቅርንጫፍ 3ኛ በመውጣት ሲያሸንፉ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1ኛ. ለቡ፣2ኛ ሰንሻይን እና 3ኛ አዋሬ ቅርንጫፎች አሸንፈዋል፡፡ከሁለተኛ ደረጃ1ኛ. ለቡ፣2ኛ. አዋሬ እና 3ኛ ቃሊቲ ቅርንጫፎች አሸናፊ ሆነዋል፡፡
በአጠቃላይ ውጤት በሳይንስና ፈጠራ ሥራ ውድድር ከቅድመ አንደኛ1ኛ. ሲኤምሲ፣2ኛ እግዚአብሔር አብ እና 3ኛ ለቡ ቅርፍነጫፎች አሸናፊ ሆነዋል፡፡ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሳይንስና ፈጠራ ሥራ 1ኛ. ሰንሻይን፣2ኛ. ወይራ እና 3ኛ. ሲኤምሲ ቅርንጫፍ ሲያሸንፍ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሳይንስና ፈጠራ ስራ ውድድር 1ኛ. ሰሚት፣2ኛ. ቃሊቲ እና 3ኛ. አዋሬ እና ለቡ አሸንፈዋል፡፡
በአጠቃላይ ውጤት አይሲቲ የፈጠራ ሥራ ዘርፍ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 1ኛ. ቃሊቲ፣2ኛ. እግዚአብሔርአብ እና 3ኛ. ለቡ ቅርንጫፍ ደረጃን ሲይዙ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 1ኛ ቃሊቲ፣ 2ኛ አዋሬ እና 3ኛ. ለቡ አሸናፊ በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በአጠቃላይ ውጤት በኪነጥበብ ዘርፍ ከቅድመ አንደኛ ደረጃ 1ኛ. ለቡ፣2ኛ እግዚአብሔርአብ እና 3ኛ ሲኤምሲ ቅርንጫፍ አሸናፊ ሲሆኑ ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 1ኛ. አዋሬ፣2ኛ. ሲኤምሲ እና 3ኛ. ሰንሻይን ቅርንጫፍ አሸናፊ በመሆን ሲያሸንፉ ከሁለተኛ ደረጃ 1ኛ. ለቡ፣2ኛ. አዋሬ እና 3ኛ. ቃሊቲ ቅርንጫፍ በዘርፉ አሸናፊነትን አግኝተዋል፡፡
በአጠቃላይ ውጤት ሥዕልና ቅርፃ ቅርፅ ዘርፍ በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል ከአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1ኛ ሲኤምሲ፣2ኛ. ለቡ እና 3ኛ. ሰንሻይን ቅርንጫፎች ሲያሸንፉ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 1ኛ. ሰሚት፣2ኛ. ለቡ እና 3ኛ. አዋሬ አሸናፊ በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

Abune Gorgorios

Abune Gorgorios

Abune Gorgorios

ለ4ኛ ጊዜ ዝግጅቱን ያስተባበረው የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ዘርፍ ይህን መሰል የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች የፈጠራ ሥራዎች እና የትምህርት ዐውደ ርእይ በቀጣይም ዓመት ከዚህ ዝግጅትና ቦታ በተሻለ ሁኔታ እንደሚያዘጋጅ ይጠበቃል፡፡