ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በርካታ አላማዎችን የያዘ አክሲዮን ማኅበር ሲሆን በአሁኑ ወቅት የትምህርት ሥራ ላይ ትኩረት በማድረግ የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶችን እያስተዳደር ያለ አክሲዮን ማኅበር ነው፡፡ አክሲዮን ማኅበሩ ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ መስፈርቱን የሚያሟሉና ብቁ የሆኑ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | የሥራ መደቡ | የትምህርት መስክ | የሥራ ልምድ |
1 | የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን | በሒሳብ፣ በባዬሎጂ፣ በኬሚስትሪ፣ በጂኦግራፊ፣ በታሪክ፣ በእንግሊዝኛ፣ በአማርኛ፣ አይሲቲ፣ስፖክን እንግሊዝ፣ስፖርት፣ግብረገብ እና በሲቪክስ የትምህርት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቀ/ች | 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰራ/የሰራች |
2 | ሳይንስ ላብራቶሪ ቴክኒሺያን | በኬሚስትሪ፣በባዬሎጂ እና በፊዚክስ ላብራቶሪ ቴክኒሺያን ዲፕሎማ/ዲግሪ የተመረቀ/ች | 4/2 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሰራ/የሰራች |
3 | ጸሐፊ I | ዲፕሎማ በሴክሬተሪያል ሳይንስ ወይም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ | 2 ዓመት እና ከዚያ በላይ |
የሥራ ቦታ፡- አዲስ አበባ
ደመወዝ፡- በስምምነት
የስራ መደቦች በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች ሲሆን ለተዘረዘሩት ክፍት የሥራ መደቦች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቶች የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃችሁን ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በአክሲዮን ማኅበሩ የሰው ሀብትና አስተዳደር ቢሮ በአካል በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
አድራሻ፡- ሰንጋ ተራ ሕብረት ባንክ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የአክሲዮን ማኅበሩ ቢሮ
ለበለጠ መረጃ:- 0964 57 27 77