አድራሻ
- +251 111 57 98 63
- it@esdros.com
- ሜክሲኮ ሕብረት ባንክ ሕንፃ 8ኛ ወለል፣ አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ኤስድሮስ ኮ.ን.ኢ አ.ማ የተሠማራባቸው ዓበይት የሦስትዮሽ የሥራ ዘርፎች
የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የታላቁን አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ ስም እና መልካም ተግባር ዋቢ በማድረግ በልጆቻቸው የተመሰረተ መሆኑ ይታወቃል። ይህ ት/ቤት ላለፉት 20 ዓመታት ገደማ ትውልድን በተሻለ ጥራት ለማፍራት እየተጋ የራሱን የጎላ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
የት/ቤቱ ታላቅ አስተዋጽኦ እንዳለ ሆኖ ትውልድ በተለያዩ መንገዶች ሃይማኖታዊ እንዲሁም ሀገራዊ ማንነቱን እየተወ እና ስነ-ልቦናዊ ተገዥነትን እያራመደ ይገኛል። ይህም ችግር እንደ ቤተ ክርስቲያንም ሆነ እንደ ሀገር ወደ ከፍተኛ ችግር እና ቀውስ እየወሰደን ይገኛል።
ይህ የገዘፈ ችግር ደግሞ በት/ቤቱ ብቻ የሚፈታ እና ለዚህ አካል ብቻ የሚተው ሳይሆን የት/ቤቱን ተማሪዎች እንዲሁም ፍሬዎች በሙሉ የሚመለከትና በኅብረት መቆም የሚጠይቅ ዓብይ ጉዳይ ነው። ስለሆነም እኛ የዚህ ት/ቤት የቀድሞ ተማሪዎች በማኅበር በመደራጀት በተቻለን አቅም የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማድረግ ተገቢ ነው።
ይህ የማኅበሩ የመተዳደሪያ ደንብ ረቂቅ ት/ቤታችንን በበላይነት ከሚመራው ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ጎን በአንድነት በመቆም የቤተ-ክርስቲያናችንን እንዲሁም የሃገራችንን ችግር ለመቅረፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ለማገዝና የድርሻችንን ለመውጣት በት/ቤቱ አነሳሽነት ብሎም በተማሪዎች በጎ ፈቃድ በመሰብሰብ በአቡነ ጎርጎሪዮስ የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር ስም መመርያ የሚሆን ነው።
በሥነ-ምግባራቸውና በትምህርታቸው መልካም ስም ያላቸው የማህበሩ አመራሮች
በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2008 ተመራቂ
በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ የተመረቀ ሲሆን በተጨማሪም በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ተማሪ
በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2009 ተመራቂ
በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዮኒቨርስቲ በስነ ህንፃ ትምህርት 5ተኛ ዓመቷን በመማር ላይ ትገኛለው
በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2012 ተመራቂ
በአሁኑ ሰዓት የሁለተኛ ዓመት የፋርማሲ እንዲሁም የሁለተኛኛ ዓመት የቢዝነስ አድምኒስትሬሽን ተማሪ
በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2008 ተመራቂ
በአግሮ ኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪዋን ያገኘች ሲሆን በቢዝነስ አድሚንስትሬሽን በማስተርስ ፕሮግራም ተማሪ
በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2011 ተመራቂ
በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ የ3ኛ ዓመት ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ተማሪ
በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2009 ተመራቂ
የአውሮፕላን ሞተር ጥገና ባለሙያ፣ በኢኮኖሚክስ ዲግሪ ምሩቅ እና 3ኛ አመት ኮምፒውተር ኢንጅነሪንግ ተማሪ
በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2008 ተመራቂ
በኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ምህንድስና ምሩቅ
በአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤት የ2009 ተመራቂ
AHUN የሚባል ድርጅት ውስጥ የማርኬቲንግ ተጠሪ ( Marketing representative)
Esdros Construction, Trade and Industry S.C.. All Rights Reserved.