የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሞዴል ፈተና በዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ይገኛል፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሞዴል ተፈታኝ ተማሪዎችን 4 ኪሎ በሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ እያስፈተነ ይገኛል፡፡
ተማሪ ተፈታኞቹ ልክ ሀገር አቀፍ ፈተናውን በሚወስዱበት ሞዴል መሠረት በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲው ውስጥ በአዳሪነት በመግባት ለዋናው አገር አቀፍ ፈተና በሚደረገው ሂደት መሠረት እየተከናወነ መሆኑ ታውቋል፡፡
ተማሪዎቹ ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ እስከ ፊታችን ቅዳሜ ድረስ በዩንቨሪስቲው የሚቆዩ ሲሆን የሞዴል ፈተናቸውን ከዕሮብ ጀምረው እስከ ቅዳሜ ድረስ የሚወስዱ ይሆናል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ተገኝተን ያነጋገርናቸው ተማሪዎች እንደገለጹልን ይህንን እድል ያመቻቸውን አቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህት ቤቶችን ያመሰገኑ ሲሆን ተማሪዎች “ከቤተሰብ ተነጥለን እንደዚህ ለዋናው ሀገር አቀፍ ፈተና ሁኔታውን እንድንለምደው እና በዚህ ዩኒቨርሲቲ የሞዴል ፈተናዎችን መፈተናችን በስነልቦና እና በሁለንተናዊ ዝግጅት እንድናደርግ ያግዘናል” ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውን ይህንን መሰል መርሀግብር የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚን ጨምሮ የማኔጅመንት አባላት እና የትምህርት ዘርፍ ኤክሰፐርቶች ፣ርዕሳነ መምህራን እና መምህራን በዩኒቨርሲቲው በመገኘት ተማሪዎቹን ያበረታቱ ሲሆን ሂደቱንም ጎብኝተዋል፡፡
ቁጥራቸው ከ190 በላይ የሆኑት ተፈታኝ ተማሪዎች የተፈጥሮ ሳይንስ እና የማኅበራዊ ሳይንስ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ2015ዓ.ም የሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች በዋናው ፈተናም አመርቂ ውጤት ለማስመዝገብ መዘጋጀታቸውን ከተማሪዎቹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

Abungorgorios