በ2015 ዓ.ም በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተዘጋጀ የዕውቅና እና ሽልማት መርሐ-ግብር ላይ በ2015 ዓ.ም ሚኒስትሪ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡
በዚሁ መርሐ-ግብር ላይ በ2015 ዓ.ም ተማሪ ባሮክ ቴዎድሮስ 99.99%፣ ተማሪ አቤሜሌክ መለሰ 99.98% እና ተማሪ መክሊት ሰለሞን 99.98% ከ6ኛ ክፍል እንዲሁም ሰበነማርያም ዳንኤል ከ8ኛ ክፍል 99.97% ውጤት በማስመዝገብ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ተማሪዎቹ ሽልማት የተበረከተላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ 30ኛው ከተማ አቀፍ የትምህርት ጉባዔ በማጠናቀቂያ መርሐ-ግብር ላይ ዓመቱን በስኬት ላጠናቀቁ አካላት ዕውቅና ለመስጠት በተዘጋጀ መድረክ ላይ መሆኑን ከከተማው አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በመረሐ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የዕውቅና ሥነ-ሥርዓቱ በተማሪዎች መካከል ጤናማ ፉክክር የሚፈጥር መሆኑን ገልፀው ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የነገ የኢትዮጵያ ተስፋ ለሆኑ ተማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አቧሬ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆኑት ተማሪ ባሮክ ቴዎድሮስ እና ተማሪ አቤሜሌክ መለሰ፣ ከሲኤምሲ ቅርንጫፍ ተማሪ ሰበነማርያም ዳንኤል እና ተማሪ መክሊት ሰለሞን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ከዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እጅ የታብሌት እና ሰርተፍኬት ሽልማት ተበርክቶላቿዋል፡፡

የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::