የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ተሸለመ!

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ጳጉሜ 6 ቀን 2015 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በተዘጋጀው የእውቅና እና ሽልማት መርሐ ግብር በ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ በክፍለ ከተማው የግል ትምህርት ተቋም 100% ተማሪዎችን በማሳለፍ 1ኛ ደረጃ በማምጣት ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
ሰኔ 26 እና 27 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በተሰጠው የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና 120 ተማሪዎችን ያስፈተነው በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የለቡ ቅርንጫፍ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ካሉ ትምህርት ቤቶች መካከል በ8ኛ ክፍል ፈተና የላቀ ውጤት በማስመዝገብ እና 100% ተማሪዎችን በማሳለፍ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

 

Abune GorgoriousAbune Gorgorious