ለመምህራን ሥርዓተ ትምህርት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች መምህራን ሥርዓተ ትምህርቱን ውጤታማ ማድረግ በሚያስችሉ ርዕስ ጉዳዮች ላይ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዓላማ መምህራን ሥርዓተ ትምህርቱን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ተገቢ ክህሎት እንዲኖራቸውና የተቃና አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስችል ሲሆን ቁጥራቸው 86 የሚደርሱ መምህራን የተሳተፉበት በ5 ርዕሳን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጥተዋል፡፡
በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ፈለቀ ስልጠናውን በማስመልከት ባደረጉት ንግግር “በዚህ ስልጠና ከፍተኛ ዕውቀት እና ተሞክሮን እንዳገኛችሁበት ይታመናል፡፡ ከእናንተ ደግሞ ያገኛቹህትን ክህሎት በተግባር በማዋል ከፍተኛ ለውጥ ለማምጣት እንድትሰሩ አደራ ማለት እፈልጋለሁ” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከጥር 27 እስከ ጥር 30 ቀን 2016ዓ.ም ለአራት ተከታታይ ቀናት በተሰጠው ስልጠና የአሰልጣኞቹና የሰልጣኞቹ ጥምረት ከፍተኛ እንደነበር ከስልጠናው ተሳታፊዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡