የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎችን አስመረቁ፡፡
አስር ቅድመ አንደኛ ደረጃ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በ2016 ዓ.ም የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ያጠናቀቁ ቁጥራቸው 2049 የሆኑ ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ፣ በባህዳር፣ በድሬደዋ እና ወልዲያ በሚገኙ ቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች በተካሄደው የምርቃት መርሀግብር ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ወላጆች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት የተካሄደ የምረቃ ፕሮግራም ሲሆን በምረቃ መርሀግብሩም ተማሪዎች ለምረቃ መርሀግብሩ ያዘጋጁበትን ዝማሬዎች፣ በገና ድርደራ፣ በተለያዩ በኢትጵያ ቋንቋዎች የእንኳን ደህና መጣቹ መልክት፣ ልዩ ልዩ መነባንብ፣ ድራማ፣ ቅኔ፣ ግጥም፣ እንቆቅልሽ እና ወረብ ካቀረቧቸው ዝግጅቶች ይገኙበታል፡፡