በኮሪደር ልማት ምክንያት ወደ መሪ የተዛወረው ሲኤምሲ ቅርንጫፍ የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሥራውን በይፋ ጀመረ

በኮሪደር ልማት ምክንያት ወደ መሪ የተዛወረው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ የ2017 ዓ.ም ማብሰሪያ መርሐግብር የኤስድሮስ ማኔጅመንት አባላት፣ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም የትምህርት ኤክስፐርቶች በተገኙበት በደማቅ የመክፈቻ መርሐግብር ተከፈተ፡፡

Abune Gorgorios

መስከረም 20 ቀን 2017 ዓ.ም በአጭር ጊዜ ግንባታው ተጠናቆ ለመማር ማስተማር ምቹ የሆነው የሲኤምሲ መሪ ት/ቤት የትምህርት ሥራውን መጀመሩን ያበሰሩት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ፈለቀ እንደተናገሩት “በሲኤምሲ አካባቢ በተካሄደው የኮሪደር ልማት ምክንያት በአጭር ጊዜ ይህንን ቦታ አግኝተን ምቹ ለማድረግ ሰፊ ርብርብ በመደረጉ ለዚህ ቀን መድረስ ችለናል፡፡ ለዚህ መሳካት በየደረጃው ያሉ ከኩባንያው አመራር እስከ መንግሥታዊ ተቋማት ላደረጉት ትብብር ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ለዘገየውም የመማር ማስተማር ጊዜ ለማካካስ እንሠራለን፡፡” ብለዋል፡፡ አቶ አንተነህ አክለውም ወላጆች ላደረጉት ትግስትና ሁለንተናዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Abune Gorgorios

ከቅድመ መደበኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ከ3200 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተማር አቅም ያለው ሲኤምሲ መሪ ቅርንጫፍ ት/ቤት ከመክፈቻ መርሐግብሩ በኋላ ተማሪዎች መደበኛውን የ2017 ዓ.ም ትምህርት በሙሉ ቀን መከታተል ጀምረዋል፡፡

Abune Gorgorios

  

 

ሲኤምሲ መሪ ቅርንጫፍ ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ ካሉት የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች በአጭር ጊዜ ለመማር ማስተማር ምቹ በመሆን እና ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተማሪዎችን በመቀበል ቀዳሚ ሆኗል፡፡

Abune Gorgorios