ከ 22 በላይ ቅርንጫፎች

የአቡነ ጎርጎርዮስ ት/ቤቶች ቅርንጫፎች

አዋሬ ቅርንጫፍ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ በ2007 ዓ.ም. በኤስድሮስ ኮ.ን.ኢ አ.ማ ሥር ሥራውን የጀመረ ሲሆን ከቅድመ መደበኛ እስከ መሰናዶ ድረስ ትምህርት እየሰጠ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ በ2014 የትምህርት ዘመን 2 ሺህ 336 ተማሪዎችን በ147 መምህራን እና በ46 የአስተዳደር ሠራተኞች በመታገዝ እያስተማረ ነው።ትምህርት ቤቱ በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ልዩ ቦታ አዋሬ የቀድሞ እንሳሮ ሆቴል ተብሎ በሚጠራው ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ቀበና መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ይገኛል።

ሲኤምሲ ቅርንጫፍ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ በ2008 ዓ.ም. የተመሠረተ ሲሆን በ2014 የትምህርት ዘመን ከቅድመ መደበኛ እስከ 11ኛ የክፍል ደረጃዎች ትምህርት እየሰጠ ይገኛል። በትምህርት ዘመኑ 2 ሺህ 83 ተማሪዎች ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት ይህ ት/ቤት 103 መምህራን እና 54 የአስተዳደር ሠራተኞችን በመያዝ ዕውቀትን ከሥነ ምግባር ጋር ለተተኪ ትውልድ እያደረሰ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ቅርንጫፍ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው ከአያት ወደ መገናኛ ሲሄዱ ሲኤምሲ አደባባይ በስተቀኝ በኩል የሚገኝ ሲሆን ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ደግሞ በዚሁ ክ/ከተማ ሰሚት ኆኅተ ምስራቅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል።

ቃሊቲ ቅርንጫፍ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ቃሊቲ ቅርንጫፍ የተመሠረተው በ2012 ዓ.ም. ነው። ከቅድመ መደበኛ እስከ 8ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች ዕውቀትን እየመገበ ያለው ት/ቤቱ በ2014 የትምህርት ዘመን 1 ሺህ 921 ተማሪዎችን በ85 መምህራን እና 35 የአስተዳደር ሠራተኞች በመታገዝ ሥራውን እየሠራ ይገኛል። ት/ቤቱ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው የቀድሞው ኪንግስ ሆቴል አዲስ ከሚሠራው ስታዲየም ከፍ ብሎ ይገኛል።

ለቡ ቅርንጫፍ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ በ2007 ዓ.ም. በኤስድሮስ ኮ.ን.ኢ አ.ማ ሥር ሥራውን የጀመረ ሲሆን በ2013 የትምህርት ዘመን 2 ሺህ 199 ተማሪዎችን በ135 መምህራን እና 41 የአስተዳደር ሠራተኞች ታግዞ እያስተማረ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ የሚገኘው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው ለቡ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት ይገኛል።

ወይራ ቅርንጫፍ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወይራ ቅርንጫፍ ሥራውን የጀመረው በ2007 ዓ.ም. ሲሆን በ2014 የትምህርት ዘመን 1 ሺህ 865 ተማሪዎችን ተቀብሎ በ108 መምህራን እና 33 የአስተዳደር ሠራተኞች በመታገዝ ትምህርቱን እየሰጠ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው ከአለርት ሆስፒታል ወደ ታቦት ማደሪያ ሲሔዱ በስተግራ በኩል ይገኛል።

ሃያ ሁለት ቅርንጫፍ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሃያ ሁለት ቅርንጫፍ ሥራውን የጀመረው በ2014 ዓ.ም. ሲሆን 421 የአጸደ ሕፃናት ተማሪዎችን ተቀብሎ በ28 መምህራን እና 10 የአስተዳደር ሠራተኞች በመታገዝ ትምህርቱን እየሰጠ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ የካ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው አዲሱ ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ፊትለፊት ይገኛል።

ድሬዳዋ ቅርንጫፍ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ድሬዳዋ ቅርንጫፍ በ2012 ዓ.ም. የትምህርት ሥራን ‘ሀ’ ብሎ የጀመረ ሲሆን በ2014 የትምህርት ዘመን በ26 መምህራን እና 10 የአስተዳደር ሠራተኞች ታግዞ 500 ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል። ትምህርት ቤቱ በድሬዳዋ ከተማ ይገኛል።

ባህርዳር ቅርንጫፍ

ባሕርዳር ቅርንጫፍ ቀበሌ 14/15
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ባሕርዳር ቅርንጫ ፍ ቀበሌ 14/15 በ2009 ዓ.ም. በኤስድሮስ ኮ.ን.ኢ አ.ማ ሥር ሥራውን የጀመረ ሲሆን ከቅድመ መደበኛ-12ኛ ክፍል ለሚገኙ 2196 ተማሪዎች በ90 መምህራን ትምህርት እየሰጠ
ይገኛል።
ባሕርዳር ቅርንጫፍ አባይ ማዶ
በ2014 ዓ.ም. አዲስ ገዝተን የከፈትነው ት/ቤት ሲሆን ከቅ/መደበኛ-6ኛ ክፍል 383 ተማሪዎችን በ27 መምህራን እያስተማርን እንገኛለን።