ለቡ ቅርንጫፍ የጥያቄና መልስ ውድድር አሸናፊ ሆነ፡፡

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የለቡ ቅርንጫፍ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ አዘጋጅነት በተካሄደ በጠቅላላ ዕውቀት የጥያቄና መልስ ውድድር ሁለተኛ በመሆን አሸናፊ ሆኗል፡፡
በ2016ዓ.ም ለሚከበረው በሀገር አቀፍ ደረጃ 18ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀንን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የጸረ ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ የጥያቄና መልስ ውድድር እንደነበር ታውቋል፡፡

ኅዳር 13 ቀን 2016ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከከል በተዘጋጀ በጠቅላላ እውቀት ላይ መሠረት ባደረገው የጥያቄና መልስ ውድድር በክፍለ ከተማው ከሚገኙ 15 ወረዳዎች በክፍለ_ከተማ_ደረጃ በነበረው ውድድር ተማሪ ብሌን ጥላሁን 2ኛ በመውጣት ተሸላሚ ሆናለች፡፡
ተማሪ ብሌን ጥላሁን ህዳር 11 ቀን 2016ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በወረዳ 01 ትምህረት ጽ/ቤት በወረዳው በሚገኙ ዘጠኝ የመንግስት እና የግል ትምህርት ተቋማበአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የለቡ ቅርንጫፍ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት በ2016
ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በተካሄደ የጥያቄና መልስ ውድድር በወረዳ ከተማ ደረጃ አንደኛ በመውጣቱ ነበር ወደ ክፍለ ከተማ ውድድር ያቀናችው፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታlተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Abune Gorgorios