የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ በፈጠራ ሥራ 1ኛ ሆነ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በወረዳው ከሚገኙ 16 ትምህርት ቤቶች ጋር በነበረው ውድድር በሒሳብ ትምህርት እና በሳይንስ ፈጠራ ውድድር በውረዳው ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል 1ኛ በመውጣት አሸንፏል፡፡
ሚያዝያ 6 ቀን 2016 ዓ.ም በተዘጋጀው ውድድር ተማሪ በአምላክ ነጋሽ በኮምፒውተር ሶፍትዌር ፈጠራ ሥራ 1ኛ በመሆን ሲያሸንፍ ፤ ተማሪ ሄሜን መዝገቡ በሒሳብ ትምህርት ዘርፍ 1ኛ በመሆን አሸናፊ ሆናለች፡፡

Abune Gorgorios

በአጠቃላይ ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ሥር ከሚገኙ 16 ትምህርት ቤቶች መካከል 1ኛ በመውጣት ወድድሩን በበላይነት በመምራት በሰፊ ልዩነት አሸናፊ ሆኗል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሲኤምሲ ቅርንጫፍ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሥር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል ለሚደረገው የአሸናፊዎች አሸናፊ በሳይንስ ዘርፍ የፈጠራ ውድድር ላይ ወረዳውን በመወከል ይሳተፋል፡፡