ለወላጆች፣ለመምህራን እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሥልጠና ተሰጠ፡፡

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወላጆች ፣ለ12ኛ ክፍል መምህራን እና ለ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዓለማ ያደረገው የ2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎቻችን ውጤታማ ለማድረግ መምኅራን፣ተማሪዎችና ወላጆች ለውጤታማነቱ ያላቸውን ድርሻ ተገንዝበው በጋራ እንዲሰሩ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡
ቁጥራቸው ከ200 በላይ የሚሆኑ የለቡ፣የአቧሬ እና የሰሚት ቅርንጫፍ የ2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች፣ከ150 በላይ ወላጆች እና ቁጥራቸው ከ30 በላይ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል መምህራን በስልጠናው ተሳትፈዋል፡፡

Abune Gorgorios

ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ስልጠናውን የሰጡት አቶ ዮናስ ግርማ “Techniques of dealing with SAT questions. አቶ ዮሴፍ በቀለ “Motivational Presentation” እና አቶ ወንድዮ ከበደ “Student’s Preparation for National Exam; Managing Possible Test Anxiety of Students, Psychological Readiness, etc.” ስልጠናዎችን ሰጥተዋል፡፡
ለመምህራን እና የትምህርት ኤክስፕርት ባለሙያዎች የተሰጡ ስልጠናውን የሰጡት ዶ/ር ታምሬ አንዱዓለም “Assessing and Evaluating Students Best /How to Prepare Standardized Tests and Assess Students.”፣በ አቶ ዮሴፍ በቀለ “Motivational Presentation” እና አቶ ሽመልስ ገበየሁ “Preparing National Exam taking Students in a fast Track Approach.”ርዕሶች ላይ ስልጠናዎችን ሰጥተዋል፡፡
ሌላው በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አዳራሽ የተሰጠው ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወላጆች ሲሆን በአቶ ዮናስ ተገኝ “How Parents can Manage test Anxiety and Related issue of their Respective Children” እና ”Managing Behaviors of age 17-19 Children towards Realizing Envisaged Goals.” በሚል ርእሰ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ ስልጠና ነው፡፡

Abune Gorgorios

በግራንድ ኤሊያና ሆቴል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል መምህራን እና ለትምህርት ዘርፍ ባለሙያዎች ስልጠናን በማስመልከት በሰጡት አስተያየት “ተማሪዎቻችንን በሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት እንዲያስመዘግቡ ምን መስራት አለብን የሚል የማነቃቂያ ስልጠና ነው፡፡ መምህራን መነቃቃት አለብን ይህ መነቃቃት ወደ ተማሪዎችም የሚጋባ በመሆኑ ውጤታማ እንድንሆን ያግዘናል::” በማለት ሀሳባቸውን የሰጡን መምህር ገንዘቤ ገለታው ሲሆኑ” ለመምህራን የሚሰጡ ስልጠናዎች በዚህ መልኩ ሲሆኑ እጅግ በጣም ደስ ይላል፡፡ በቀጣይም ምን መስራት እንዳለብን ያየንበት ስልጠና ነው፡፡ ያሉት መምህር ተመስገን እሸቴ በአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች የአቧሬ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤት የባዮሎጂ መምህር ናቸው፡፡ ሌላኛው ሀሳባቸውን ያጋሩን የሰሚት የእንግሊዘኛ መምህሩ መምህር ተስፋዬ እርገጤ እንደተናገሩት “ስልጠናው እኛ የተማሪዎቻችንን ውጤታመነት ለማረጋገጥ ከዚህ በፊት ከነበሩ ውጤቶች በተሻለ እንዲያመጡ እና ወደፊትም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ምን መስራት እንዳለብን የሚያሳይ ነው” በማለት ገልጸዋል፡፡

Abune Gorgorios

ሌላኛው አስተያየታቸውን የሰጡት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የለቡ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነው ተማሪ አቤል ሚካኤል “…እንዴት ጊዜያችንን መጠቀም እንደምንችል የሚያሳይ ነው፡፡” በማለት ሀሳቡን የሰጠን ሲሆን የአቧሬ ቅርንጫፍ የሆነችው ተማሪ ራኬብ ተመስገን “ስልጠናው አስተማሪና መንፈስን የሚያነቃቃና ለማጥናት የሚያግዘን ነው ብላለች፡፡” የሰሚት ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነችው ኤፍራታ ቴዎድሮስም በበኩሏ “በስልጠናው እንዴት አዕምሮአችንን መጠቀም እንደምንችልና ውጤት ላይ መድረስ እንደምንችል የሚያሳይ ነው፡፡” በማለት ሀሳቧን ገልጻለች፡፡

Abune Gorgorios

ስልጠናውን በተመለከተ አስተያየታቸውን የሰጡት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ወላጆች በበኩላቸው “ይህንን ስልጠና በማግኘቴ በጣም ዕድለኛ ነኝ፡፡ ብዙ የጎደሉኝ ነገሮች እንዳሉኝ በስልጠናው ያየሁበት ነው፡፡ እንደዚህ አይነት ስልጠና ቢቀጥል ጥሩ ነው፡፡” በማለት ሀሳባቸውን ያካፈሉን በለቡ ቅርንጫፍ ልጆቻቸውን እያስተማሩ የሚገኙት አቶ አለማየሁ አያሌው ሲሆኑ ሶስት ልጆቻቸውን በአቡነ ጎርጎርዮስ እያስተማሩ የሚገኙት አቶ ዬናስ ታደሰ “ጥሩ ስልጠና ነው፡፡ ያነቃቃል ለልጆቻችን ጥሩ ድጋፍ እንድናደርግ የሚያደርግ ነው፡፡ በዚህ ቢቀጥል መልካም ነው፡፡” ያሉ ሲሆን እኛና ልጆቻችን ምን ያህል ተራርቀን እንዳለን የሚያሳይ ነው፡፡ልጆቻችንን እንዴት አድርገን መያዝ እንዳለብን የሚያሳይ ነው፡፡የተሻለ ውጤት እንድናመጣ የሚያስችል ስልጠና ነው፡፡” በማለት ሀሳባቸውን የሰጡን የሰሚት ቅርንጫፍ የወላጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሰፍነ ተረፈ ናቸው፡፡ይንን መሰል ስልጠናዎች አነቃቂና መነሳሳትን እንደፈጠረባቸው ከተሳታፊዎች ለምዳት ተችሏል፡፡

Abune Gorgorios