ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ኦንላይን/Online/ ፈተና ተሰጠ ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ1ኛ መንፈቀ ዓመት አጋማሽ ፈተና በኦንላይ በየቅርንጫፍ ትምህርት ቤታቸው አስፈተኑ፡፡
በአዲስ አበባ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ቅርንጫፍ የአቧሬ፣የለቡ እና የሰሚት ቅርንጫፍ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በ2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና መለማመድ የሚያስችላቸው እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡

Abune Gorgorous

ቁጥራቸው 216 የሚሆኑ የአቧሬ ፣የለቡ እና የሰሚት የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ ፈተናው ለሚሰጠው ሀገር አቀፍ ፈተና መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ ኦንላይ ቢሆን አሁን የወሰዱት ኦንላይን ፈተና ጥሩ ተሞክሮ የሚያገኙበት እንደሚሆን ከተፈታኝ ተማሪዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት እና የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ይህ የመጀመሪያ መንፈቅ አጋማሽ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚሰጠው ብሄራዊ ፈተና ዝግጅት መነሻ በመሆን በቀጣይ የሚደረጉ ፈተናዎች ለዚሁ ዝግጅት በሚያስችል መልኩ እንደሚሆን ታውቋል፡፡
ከታህሳስ 10 እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2016ዓ.ም ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመጀመሪያ አጋማሽ የኦንላይን ፈተና ከተወሰነ የኔትወርክ/Network / መቆራረጥ በስተቀር በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

Abune Gorgorous