ሰሚት ቅርንጫፍ ከሞዴል አፍሪካ ሽልማት ተበረከተለት ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሞዴል አፍሪካ ኢትዮጵያ አዘጋጅነት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከሚገኙ 4 ትምህርት ቤቶች ጋር አፍሪካዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በተደረገ የቃል ክርክር/ debate/ ላይ በመሳተፍ ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በተዘጋጀ “የ21ኛው ክፍለ ዘመን የአፍሪካ የልማት አቅጣጫ የወጣቶች ግብ በ2030” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀ የክርክር መድረክ ላይ የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 11 ተማሪዎች ከፍተኛ ተፎካካሪ በመሆን የተሳተፉበት እንደነብር ታውቋል፡፡
በጥር ወር መጨረሻ ሳምንት ላይ በተካሄደው አፍሪካዊ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከአዲስ አበባ የተወጣጡ 4 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል ከፍተኛ የቃል ክርክር/debate/ በማድረጉ ሰሚት 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰርተፍኬ እንደተበረከተለት ከቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ሰሚት ቅርንጫፍ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተለያዩ ውድድሮች በመሳተፍ በርካታ ሽልማት የተበረከቱለት መሆኑ ይታወሳል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Abune Gorgorios