ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለ አመራር አካላት፣ ለርዕሳነ መምህራን እና ለዕቅድ ዝግጅት ኮሚቴ አባላት በዕቅድ ዝግጅት ሂደት ላይ ሥልጠና ሰጠ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮቹ እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ ዝግጅት ላይ ለሚሳተፉ የ ዕቅድ ዝግጅት ኮሚቴ አባላት አጠቃላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናው የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የ2017 የበጀት እቅድ ወጥና ተመሳሳይ አካሄድ እንዲኖር ከቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች እስከ ዋናው መሥሪያ ቤት ተመጋጋቢና የተናበበ፣ የሚመዘን፣ ሊደረስበት የሚችል ውጤታማ የሆነ እና የግዜ ሰሌዳ የተቀመጠለት ዕቅድ ማዘጋጀት እንዲቻል ለማድረግ ታልሞ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ስልጠናውን በ3 ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን ፤ የበጀት ዕቅድ ዝግጅት ሂደት /“Master Budget”/ “የዕቅድ ዝግጅት ሂደት መምሰል ያለበት እና እንዴት ይዘጋጃል እንዲሁም የፊሲካል እና ፋይናሺያል ዕቅድ ግንኙነት እና ተመጋጋቢነት “key Awareness on fiscal and budget of its Correlation” በሚል ርዕስ ጉዳዮች ስልጠናዎች ተሰጥተዋል::

Esdros Construction 

የስልጠናው ተሳታፊዎች ከዚህ በፊት የነበረው የበጀት እቅድ ዝግጅት ቁልፍ ችግሮች፣ የመፍትሄ ሀሳቦች እና የ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጀት ምን ቅርጽ ሊኖረው ይገባል በሚሉ ርዕሳነ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል፡፡
ባለፈው ቅዳሜ መጋቢት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጠው ስልጠና ላይ 32 የሚሆኑ የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ከፍተኛ አመራር አባላት፣ርዕሳነ መምህራን እና መካከለኛ አመራር አካላት የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናው ለ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ ዝግጅት ትልቅ ግብዓት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Esdros constructionEsdros construction