በአራዳ ክፍለ ከተማ አዋሬ ቅርንጫፍ 1ኛ ሆነ፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት መካከል በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ በክፍለ ከተማው ውድድሩን 1ኛ በመውጣት አጠናቋል፡፡
በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል በውድድሩ 1ኛ የወጣ ሲሆን ተማሪ ኄራን አለማየሁ በውድድሩ 2ኛ ሆናለች፡፡
ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል ከ6ኛ ክፍል 1ኛ እና ተማሪ ኄራን አለማየሁ ከ8ኛ ክፍል 2ኛ በመውጣት በአራዳ ክፍለ ከተማ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች መካከል ቀዳሚ ሆነዋል፡፡

Abune Gorgorios

ታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 7 በተካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል እና ተማሪ ኄራን አለማየሁ በውድድሩ 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ፣የሜዳሊያና ሰርተፍኬት ተሸላሚ እንደነበሩ ይታወሳል፡፡
ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል በቀጣይ አራዳ ክፍለ ከተማን በመወከል በአዲስ አበባ ደረጃ ለሚካሄደው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ይወዳደራል፡፡