በአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል በቀለም ትምህርት የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር በ6ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከከል ተካሄደ፡፡
ጥር 4 ቀን 2016ዓ.ም በተካሄደው የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር በሰባት የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል ሲሆን ውድድሩም እጅግ ፉክክር የበዛበት እንደነበር ታውቋል፡፡

Abun Gorgorios

በአቡነ ጎርጎርዮስ ወይራ ቅርንጫፍ አዘጋጅነት በተካሄደው የ6ኛ ክፍል በ5 የትምህርት ዓይነቶች የጥያቄናመልስ ውድድር ተማሪ ሊዲያ ለይኩን ከለቡ 1ኛ ስትውጣ ተማሪ አርሴማ እንዳወቅ ከሲኤምሲ እና ተማሪ ብሌን ጥላሁን ከለቡ 2ኛ እና 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል፡፡በውድድሩም በትምህርት ቤቶች ደረጃ በ6ኛ ክፍል ለቡ ቅርንጫፍ 1ኛ የወጣ ሲሆን ሲኤምሲና ወይራ ቅርንጫፍ 2ኛ እና 3ኛ በመውጣት መሪነቱን ያዘዋል፡፡
በ8ኛ ክፍል የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል በ7 የቀለም ትምህርት የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ እዩኤል ሽመልስ ከለቡ ቅርንጫፍ ውድድሩን 1ኛ በመውጣት የመራ ሲሆን ከወይራ ቅርንጫፍ ተማሪ ሱራፌል አየነው እና ተማሪ ትዕምርት ደርቤ 2ኛ እና 3ኛ በመውጣት አሸንፈዋል፡፡ በትምህርት ቤት ደረጃ በ8ኛ ክፍል 1ኛወይራ፣ 2ኛ ለቡ እና 3ኛ አዋሬ ቅርንጫፍ በመውጣት አሸንፈዋል፡፡
የ2016ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር በአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል የ6ኛና የ8ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል ተወዳዳሪነትን ከመፍጠሩም በላይ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል ጠንካራ ግንኙነትን የሚፈጥር መሆኑን ከአዘጋጆቹ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Abune Gorgorios