በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ 615 ውጤት ተመዘገበ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነው ናሆም መርሻ በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና 615 በማምጣት ከቀዳሚዎች መካከል መሆን ችሏል፡፡
በ2015 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሄራዊ ፈተና ከወሰዱ 845 ሺህ 188 ተማሪዎች ውስጥ 27 ሺህ (3.2%) ተማሪዎች ብቻ ከ50 በመቶ በላይ በማምጣት የማለፍያ ውጤት ማስመዝገባቸው ይታወሳል፤ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ0.01 መቀነሱን ያሳያል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመዘገበው ከፍተኛ ውጤት 649 ከ700 በተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት መስክ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሲሆን በማኅበራዊ ሳይንስ ደግሞ 533 ከ600 ከፍተኛ ውጤት ሆኖ በወንድ ተማሪ መመዝገቡ ይታወቃል፡፡
በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ 3 ሺህ 106 ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ በሆነው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ለቡ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆነው ተማሪ ናሆም መርሻ ከተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት ከ 700 615 በማምጣት ከፍተኛ ውጤ በማስመዝገቡ የተሰማንን ታላቅ ክብርና ደስታ እየገለጽን ለመላው የተቋሙ ማኅበረሰብ በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!! እንላለን፡:Abune Gorgorios