በ2015 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም እና በ2016 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የዋና መሥሪያ ቤት ሠራተኞች በ2015ዓ.ም ዕቅድ አፋጻጸም እና በ2016ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት አካሄዱ፡፡
ጥቅምት 24 ቀን 2016ዓ.ም በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በወይራ ቅርንጫፍ አዳራሽ በተካሄደው የ2015ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ሪፓርት ላይ እና በ2016 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

  Esdros Construction

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የዕቅድ ዝግጅትና ግምገማ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ እንዳለ ተሾመ የ2015ዓ.ም አፈጻጸም እና የ2016ዓ.ም ዕቅድን ለሠራተኞች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በቀረበው ረፖርትም የተማሪዎችን ቅበላና ምዝገባን በ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት በድምሩ 17,208 ተማሪዎችን ለመመዝገብ ታቅዶ 16,736 (97%) ተከናውኗል፡፡1 አዲስ ትምህርት ቤት ለመክፈት ታቅዶ የቃሊቲ ትምህርት ቤት ግዥ ተከናውኗል፡፡ 2 አዲስ ትምህርት ቤቶችን ለመክፈት ታቅዶ የሰንሻይን ቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ተከፍተው ምዝገባ መከናወኑን፡፡በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ለ1,747 ርዕሳነ መምህርን፣ ለመምህራን ለኃላፊዎች እንዲሀም ለአስተዳደር ሠራተኞች ስልጠና ለመስጠት ታቅዶ ተሠጥቷል፡፡

ለግማሽ ቀን በቆየው የ2015ዓ.ም ዕቅድና አፈጻጸም እና በ2016ዓ.ም ዕቅድ ትውውቅ መርሐ-ግብር ላይ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን የየስራ ክፍል ኃላፊዎችም ማብራሪያና ገለጻ አድርገዋል፡፡