አዋሬ ቅርንጫፍ በ6ኛና በ8ኛ ክፍል 1ኛ ወጣ ፡፡

በአራዳ ክፍለ ከተማ በወረዳ 7 ትምህርት ጽ/ቤት አዘጋጅነት በወረዳው ከሚገኙ 18 የመንግሥትና የግል ትምህርት ተቋማት መካከል በተደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ 1ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቋል፡፡
በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በብሔረ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አዳራሽ በተካሄደው የጥያቄና መልስ ውድድር የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ ተማሪ የሆኑት ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል እና ተማሪ ኄራን አለማየሁ በውድድሩ 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ፣የሜዳሊያና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

abune Gorgorios

የ6ኛ ክፍሉ ተማሪ እስጢፋኖስ ሱራፌል እና የ8ኛ ክፍሏ ተማሪ ኄራን አለማየሁ በቀጣይ በክፍለ ከተማ ደረጃ በሚደረገው ውድድር የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7ን በመወከል ይወዳደራል፡፡
የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች አዋሬ ቅርንጫፍ ተማሪዎች በቀረቡበት ውድድሮች በከፍተኛ ብልጫ በማሸነፍ የሚታወቁ ሲሆን በ2015 ዓ.ም በነበሩ ውድድሮችም በወረዳው በቀዳሚነቱ ይታወቃል፡፡

የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::