ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በልዩ ቅናሽ አክሲዮን ለሽያጭ አቀረበ

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ በበርካታ አዳዲስ የኩባንያችን ባለአክሲዮን ለመሆን ፍላጎት ባላቸው ደንበኞቹ ጥያቄ መሰረት እስከ ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ብቻ የሚቆይ አዳዲስ አክሲዮኖችን እንደሚሸጥ ነው ያስታወቀው፡፡

ዘመኑን በዋጁ 12 ባለ አክሲዮኖች በብር 100 ሺህ ተመስርቶ በአሁኑ ወቅት ከ3750 በላይ ባለ አክሲዮኖች ያቀፈው ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ አዳዲስ አክስዮኖችን በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

Esdros Construction

በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ እና በዋናዋና የክልል ከተሞች በ27 የአቡነ ጎርጎሪዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ከ19 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ የሚገኘው ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የአቡነ ጎርጎሪዮስ ትምህርት ቤቶች ተፈላጊነት ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በመምጣቱ ተደራሽነቱን ለመጨመር እና ጥራት ያለው የትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲቻል አዲስ ት/ቤቶቹን መክፈት እና ያሉትንም ማስፋፋት ተገቢ በመሆኑ ለትምህርቱ ዘርፍ እገዛ ለማድረግ እንዲያስችለን እና አዳዲስ የቢዝነስ እሳቤዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በተለምዶ 22 አካባቢ አክሱም ሆቴል ጀርባ 3B + G + 15 ወለል ያለው ለቅይጥ አገልግሎት የሚውል የመኖሪያ አፓርታማ በመግንባት ላይ የሚገኝ ሲሆን በአሁኑ ግዜ የእስትራክቸራል ስራው ተጠናቋል፡፡

Esdros Construction

አክሲዮን ማኅበሩ ባለፉት 5 ተከታታይ ዓመታት 29 በመቶ በዓመት ትርፍ ያስመዘገበ ከመሆኑም በላይ፣ በአሁኑ ወቅት የጠቅላላ ሀብት መጠኑን 1 ቢሊዮን ብር ያደረሰ ኩባንያ መሆኑ ተመራጭ አድርጎታል፡፡

ይህንን ተግባር የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ፣ እንዲሁም የተቋሙን ባለአክሲዮን የመሆን ፍላጎት ባላቸው በ አዳዲስ ዕጩ ባለአክሲዮኖች ጥያቄ መሰረት ቀድሞ የነበረውን ዝቅተኛ የአክሲዮን ሽያጭ መጠን ከ100 አክሲዮን ወደ 50 አክሲዮን ዝቅ ተደረጎ የአክሲዮን ሺያጭ በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በመሆኑም የአክሲዮን ጉዳዮችን በተመለከተ መረጃ ለማግኘት፣ የኩባንያውን የኮርፖሬት ማርኬቲንግ እና ንግድ ልማት መምሪያ በስ.ቁ +251 157-59-54/0930-36-37-79 /0973-60-00-10 በመደወል አክሲዮን በመግዛት የኩባንያ ባለቤት እንዲሆኑ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

Esdros Construction Esdros constructon