ከፍለው መማር ለማይችሉ ተማሪዎች ነጻ የትምህርት እድል ተሰጠ፡፡

ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች የትምህርት ዘመኑን የትምህርት ክፍያ ከፍለው መማር ላልቻሉ 73 ተማሪዎች የነጻ ትምህርት እድል ሰጠ፡፡

ቁጥራቸው 73 የሆኑ ተማሪዎች በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ወላጆቻቸው በተለያየ ምክንያት የትምህርት ክፍያን ለመፈጸም በመቸገራቸው የተሰጠ የነጻ የትምህርት እድል መሆኑን ለማወቅ የተችሏል፡፡
ኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት እየሠራ የሚገኝ ሲሆን በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ወላጆች ላይ በሚገጥም ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመፍታት ልጆቻቸው ተረጋግተው እና ውጤታማ ሆነው እንዲማሩ እየሠራ ይገኛል፡፡
እነዚህም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በ15 ቅርንጫፍ ከሚገኙ ተማሪዎች መካከል ሲሆኑ በ2015ዓ.ም ለ50 ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል የተሰጠ ሲሆን በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን 23 ተጨማሪ አዳዲስ ተማሪዎችን በመጨመር ቁጥሩ 73 እንደደረሰ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ኩባንያው ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ነጻ የትምህርት ዕድል የሰጣቸውን 73 ተማሪዎችን የብር 1.3 ሚለዮን ብር የሸፈነ ሲሆን በአራዳ እና ቃሊቲ ክፍለ ከተማም ለሚገኙ አረጋውያን ድጋፍ የሚሆን ከ200 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡

 

Abune Gorgorios