ከፍተኛ ፉክክር የታየበት የ12ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል በቀለም ትምህርት የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር በ12ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከከል ተካሄደ፡፡
ጥር 9 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር የጥያቄና መልስ ውድድር በሦስት የአቡነ ጎርጎርዮስ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች መካከል ሲሆን ውድድሩም እጅግ ፉክክር የበዛበት እንደነበር ታውቋል፡፡

በኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርት ዘርፍ አዘጋጅነት በወይራ ቅርንጫፍ አዳራሽ በተካሄደው የ12ኛ ክፍል የተፈጥሮ ሳይንስ በ7 የትምህርት ዓይነቶች የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ ስምኦን ተሾመ ፣ ተማሪ ሶፎኒያስ ተሾመ እና ተማሪ ናሆም ንጉሥ ከለቡ 1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል፡፡በውድድሩም በተፈጥሮ ሳይንስ በ12ኛ ክፍል ለቡ ቅርንጫፍ 1ኛ የወጣ ሲሆን ሰሚትና አዋሬ ቅርንጫፎች 2ኛ እና 3ኛ ወጥተዋል፡፡

Abun GorgoriosAbun Gorgorios

በዚሁ ውድድር በማኅበራዊ ሳይንስ በ7 የትምህርት ዓይነቶች የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ እዩኤል ምትኩ(ከለቡ) 1ኛ፣ ተማሪ ምቋመ ማርያም(ከአዋሬ) 2ኛ እና ተማሪ አሜን ብስራት (ከአዋሬ) ናሆም ንጉሥ ከለቡ 3ኛ በመውጣት አሸናፊ ሆነዋል፡፡በውድድሩም በማኅበራዊ ሳይንስ በ12ኛ ክፍል በቅርንጫፍ ትምህርት ቤት ደረጃ አዋሬ ቅርንጫፍ 1ኛ የወጣ ሲሆን ለቡና ሰሚት ቅርንጫፎች 2ኛ እና 3ኛ ወጥተዋል፡፡

Abun Gorgorios

በውድድሩ መዝጊያ ላይ የተገኙት የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የትምህርቱን ዘርፍ የሚመሩት ምክትል ሥራ አስኪያጅ የትምህርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዘሪሁን ክብረት “ይህንን መሰል ውድድር በተወዳዳሪዎች መካከል የሚፈጥረው መንፈስ በተጨማሪ የውድድሩ ውጤት ያሉብንን የከፍተት ቦታዎች ትኩረት ሰጥተን እንድንሰራ የሚያደርግ ነው” ብለዋል፡፡

Abun Gorgorios

የ2016 ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ውድድር በአጠቃላይ በ12ኛ ክፍል የጥያቄና መልስ ውድድር 1ኛ በመውጣት ለቡ ቅርንጫፍ ሲያሸንፍ አዋሬና ሰሚት 2ኛ እና 3ኛ በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በመርሐግብሩ ማብቂያ ላይ ውድድሩን ላሸነፉ ተማሪዎች እና ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ልዩ ልዩ ሽልማቶችና ሰርተፍኬት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

Abune Gorgorios