ወላጆች ከመምህራን ጋር ስለ ልጆቻቸው የሚወያዩበት መርሀግብር ተካሄደ፡፡

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በአዲስ አበባ በሚገኙ 18 ቅርንቻፍ ትምህርት ቤቶች ወላጆች ከመምህራን ጋር ስለ ልጆቻቸው አጠቃላይ ጉዳይ የሚመክሩበት መርሀግብር በቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች ተካሄዷል፡፡
ታህሳስ 20 ቀን 2016 ዓ.ም አላማውን በልጆች የትምህርት ውጤት እና በልጆች ስነምግባር እና የትምህርት ቤት አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ያተኮረ በገጽለገጽ ወላጅ ከመምህራን ጋር የሚወያይበት በውይይቱም ጠንካራ ጎን የሚጎለብትበትን እና ትግሮች ደግሞ በጋራ መፍትሄ የሚበጅለትን አላማ ለማሳካት ያለመ ዝግጅት ነበር፡፡

ይህንን መሰል መርሀግብር በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በሁሉም ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የተለመደና ባህል መሆኑ የተገለጸው፡፡ የወላጆችና የመምህራን ገጽለገጽ መርሀግብር በየመንፈቅ ዓመት አጋማሽ ላይ የሚደረግ በመሆኑ ተማሪዎች መንፈቅ ዓመቱን ጥሩ ውጤት ለማስመዝገብ የወላጅ እና የመምህራን የጋራ ድጋፍን ከመፍጠሩም በላይ የክፍተት ቦታዎችን መሙላት ያስችላል፡፡
ዕለተ እሁድ ታህሳስ 20 ቀን 2016ዓ.ም በተካሄደው በዚሁ መርሀግብር ወላጆችና መምህራን ጊዜ ሰጥተው በልጆቻቸው ውጤትና ስነምግባር ላይ በጥልቀት በመወያየት በጋራ ለመስራት ጠንካራ ግንኙነት የፈጠሩበት እንደነበር ከወላጆችና መምህራን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Abune Gorgorios