የተማሪዎችን ዕለታዊ ጉዳይ መረጃ የሚሰጥ መተግበሪያ ሥራ ጀመረ፡፡

በአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን የየዕለት ጉዳዮች መረጃ የሚሰጥ መተግበሪያ ሥራ መጀመሩን የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል አስታወቀ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ያዘጋጀው ይኸው መተግበሪያ ወላጆች ስለ ልጆቻቸው የትምህርት ቤት ውሎ/ሁኔታ እና የትምህርት ጉዳዮችን ለመከታተል የሚያስችል መሆኑን ለመረዳት ተችሏል፡፡
መተግበሪያው ወላጆች የልጆቻቸውን የትምህርት ውጤት ት/ቤት መምጣት ሳይጠበቅባቸው ማየት እንዲችሉ ከማድረጉም ባሻገር ልጆቻቸው በየዕለቱ ትምህርት ቤት መገኘታቸውን እና ወሳኝ የሆኑ የቅርንጫፍ ትምህርት ቤቱን መረጃዎች ማግኘት የሚያስችላቸው ሆኖ መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡
ወላጆች በስልካቸው ላይ መተግበሪያውን በማውረድ እና በመጠቀም ብቻ የልጆቻቸውን ዕለታዊ መረጃ ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

የአክሲዮን ማኅበራችንን ድረ ገፅ https://esdros.com በመከታተል ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉ::

 

Abune Gorgorios