የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች በስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል አጋዥ መረጃዎችን አገኘ፡፡

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ከኢፌዲሪ ስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል ኢንስቲትዩት ለመማር ማስተማሪያ አጋዥ የሆኑ ከ200 በላይ የተለያዩ ካርታና ብሄራዊ አትላሶችን አገኘ፡፡

ታህሳስ 22 ቀን 2016ዓ.ም በስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል ኢንስቲትዩት በተደረገ ርክክብ ላይ የኢንስቲዩቱ ዋና ዳሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ካርታና ብሄራዊ አትላሶችን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት “ይህንን መሰል ድጋፍ በተለይ ለትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማሪ ድጋፍ በማድረጋችን በተለይ ለዛሬ ለአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ በማድረጋችን ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል” ብለዋል፡፡
ካርታና አትላሶችን የተረከቡት ቀሲስ ክፍሉ ወ/ሐዋሪያት እንደተናገሩት “የቀድሞው የካርታ ስራዎች ኤጀንሲ የአሁኑ ስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል ኢንስቲትዩት ላደረገልን ድጋፍ ከልብ ለማመስገን እንወዳለን” ያሉ ሲሆን ቁሳቁሶቹም ለየ ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶቹ ለመማር ማስተማር አጋዥ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡

Esdros construction

በስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል ኢንስቲትዩት ውስጥ “የኢትዮጵያ ልጆች የስፔሽ ክህሎት እና ጂኦሰፓሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል”የተከፈተ ሲሆን በክረምት ወቅት የስፔስ ሳይንስና ጂኦሰፓሻል ተስጥኦ ያላቸው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች በክረምት መጥተው መማር የሚችሉ መሆኑን የኢንስቲዩቱ ዋና ዳሬክተር አቶ አብዲሳ ይልማ ጋብዘዋል፡፡ ዋና ዳሬክተሩ አያይዘውም የእንጦጦ ኦርዞርባቶሪ ማዕከል ከመጋቢት ወር መጀመሪያ ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚሆን ገልጸው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችና መምህራን ቦታውን እንዲጎበኙ እንጋብዛለን ብለዋል፡፡