፲፩ኛው የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ኅዳር 30 ይካሄዳል ፡፡

የኤስድሮስ ኮንስትራክሽን ንግድ እና ኢንዱስትሪ አ.ማ 11ኛው የባለ አክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤውን ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ለማካሄድ ዝግጅት መጀመሩን አስታወቀ፡፡
ኩባንያው 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ እሑድ ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ በቀድሞው ግሎባል ሆቴል በአሁኑ ኢትዮጵያ ሆቴል ቁጥር ሁለት እንደሚካሄድ የዳሬክተሮች ቦርድ አስታውቋል፡፡

ጉባኤው የጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣ አዳዲስ ባለ አክሲዮኖችን መቀበል፣ የዲሬክተሮች ቦርድ የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ፣ የውጭ ኦዲተር ሪፖርት ፣የዳሬክተሮች ቦርድ የ2016 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎችን ፣ የዳሬክተሮች ቦርድ የ2016 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ፣የ2015 በጀት ዓመት የትርፍ ክፍፍል ላይ መወሰን፣ተተኪ የዳሬክተሮች ቦርድ አባልን ማጽደቅ፣የዳሬክተሮች ቦርድ አባላትን አበል ማጽደቅ እና የ11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡
በዚሁ ጉባኤም በ8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የ8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎችን ማጽደቅ፣የአክሲዮን ማኅበሩን መመሥረቻ ጽሑፍ ማሻሻልና ማጽደቅ እና የ8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባኤን ማጽደቅ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ ከዳሬክተሮች ቦርድ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በጉባኤው ላይ መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ጉባኤው ከመካሔዱ በፊት ሜክሲኮ ሰንጋተራ ሕብረት ባንክ ሕንፃ 8ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የአክሲዮን ማኅበሩ ቢሮ በአካል በመገኘት የውክልና ቅጽ በመሙላት ውክልና መስጠት የምትችሉ ሲሆን ተወካዮቻችሁ የውክልና ፎርሙን ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን እንዲሁም የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም የመንጃ ፈቃድ ይዘው እንዲቀርቡ በማድረግ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑ ተገልጾል፡፡

ስለ ጉባኤው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ የወጣውን ማስታወቂያ መመልከት የሚቻል መሆኑ ታውቋል፡፡

Esdros Construction