4ኛው የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች የፈጠራ ሥራና ዐውደ ርእይ ሊከፈት ነው!

Abuneg photo

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የትምህርት ዐውደ ርእይ እና የፈጠራ ሥራዎች ውድድር መርሀግብር አርብ መጋቢት 20 ቀን 2016 ዓ.ም ይከፈታል፡፡
ለ4ኛ ጊዜ በሚካሄደው የትምህርት ዐውደ ርእይ እና የተማሪዎች የፈጠራ ሥራ በኪነጥበብ፣ የተማሪ የፈጠራ ሥራ፣ ICT፣ ሥዕልና ቅርጻቅርጽ፣ የተቋሙ እሴት እና ዲኮረሽን (የተሰጠህን ቦታ ማሸብረቅና ማስዋብን) ዘርፍ ላይ ውድድር የሚካሄድበት ሲሆን ከመጋቢት 20 እስከ 22 ቀን 2016 ዓ.ም የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርት ቤቶች 27ኛ ቅርንጫፍ በሆነው ሰንሻይን አጸደ ሕፃናትና 1ኛ ደረጃ ቅርንጫፍ ይካሄዳል፡፡
በመርሐግብሩ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙት 18 ቅርንጫፍ ትምህርት ቤቶች የሚሳተፉበት ሲሆን በፈጠራ ስራዎች፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በኪነጥበብ ዘርፍ በርካታ የፈጠራ ሥራዎች የሚቀርቡበት በመሆኑ ፉክክሩም ከፍተኛ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
ለ3 ተከታታይ ቀናት ለእይታ በሚቆየው በዚህ ዐውደ ርእይ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ወላጆች፣ መምህራን እና ተማሪዎች እንደሚጎበኙት ይጠበቃል፡፡ በመሆኑም፣ እርስዎም የዐውደ ርእይው ተሳታፊ እንዲሆኑ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል፡፡